የሐረርወርቅ ጋሻው፣ ከአሜሪካን መንግስት እና ከሄርማን ኮሀን ጋር ኢትዮጵያን ካለችበት የመከፋፈል አደጋ ….

Print Friendly, PDF & Email

International Ethiopian Diplomacy Council Committee (IEDCC)

Dallas Texas

የሐረርወርቅ ጋሻው ፣ ከአሜሪካን መንግስት እና ከሄርማን ኮሀን ጋር ኢትዮጵያን ካለችበት የመከፋፈል አደጋ የሚያድን አስቸኳይ ሃሳብ በዲሲ አቀረበች።

አለም አቀፍ መግለጫ
ዲሴምበር 12 ቀን 2017

በዳላስ ቴክሳስ ንዋሪ በመሆን የምትታወቀው የሐረርወርቅ (የኢትዮጵያ ወርቅ) ጋሻው፣ ትናንት ሰኞ እንደ አውሮፓ አቆጣጠር፣ ዲሴምብር 11 2017፣ ከጠዋቱ ሶስት ሰአት ተኩል በዋሽንግተን ዲሲ ከከሀን ጋር ጭምር ባደረገችው የሁለት ሰአት ስብሰባ፣ አሜሪካን እስፓንሰር ሆና አስቸኩአይ ኮንፍራንስ ጥሪ በማድረግ ኢፒአርዲኤፍ መንግስት እና ሁሉንም እስከዛሬ ለኢትዮጵያ ልአላዊነት እና ለእውነተኛ ዲሞክራሲ በመታገል የሚታወቁትን ድርጅቶች እና መሪዎቻቸውን ያካተተ ስብሰባ አሜሪካን እስፓንሰር እንድታደርግ ጥሪዋን በ International Ethiopian Diplomacy Council Committee እና በራስዋ ስም አቅርባለች።

የቀድሞው የአፍሪካ ጉዳይ ዋና ጸሃፊና አምባሳደር ህርማን ኮን በበኩላቸው የኢትዮጵያን መከፋፈል በአሁኑ ጊዜ እሳቸውም ይሁኑ የአገራቸው መንገስት አሜሪካን እንደማይደግፍ እና ኢትዮጵያ አንድነትዋን ጠብቃ እንድትኖር በበኩላቸው መፍትሄ ይሆናል ብለው ስለሚያስቡትም በዝርዝር በመናገር አሜሪካን ኮንፍራንስ እንድታደርግ የበኩላቸውን እንደሚተባበሩ እና ጥሩ ሃሳብ መሆኑንም ለየሐረርወርቅ ቃል ገብተዋል።

ቀጥላም በሰፊው ከተነጋገረችበት አጀንዳ በአማራው ሕዝብ ላይ ኢትዮጵያን ለመከፋፈል ሲባል የተደረገውን የአማራውን ብሄር የማጥፋት ዘመቻ በድብደባ፣ በጥይት፣ በሚንጫ፣ ጭፍጨፋ , ከሰባት ሚልየን ያላነሰ የአማራ ብሄር ተወላጅ በመለስ እና ከዛም በመቀጠል እስከ ዛሬም በየቀኑ አማራው ከያለበት እንደ ወንጀለኛ እየታደነ ከኢትዮጵያ ዙሪያ እየተመነጠረ አገሩ ጎንደር ፣ ጎጃም እና ወሎ ብቻ ይመሰል ወደ እዛ እየተባረረ መሆኑን ጭምር በማስረጃ በማቅረብ በተጨማሪም ሁለት መጽሃፎች አንዱ በሙሉቀን ተስፋው ወጣቱ ጋዜጠኛ የተፃፈ እና ቀጥሎም በደራሲ ጌታቸው ረዳ የኢትዮጵያ ሰማይ አዘጋጅ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ አንድነት ታጋይ የተፃፈ የትግራይ ብሄርተኞ በሚል በቅርብ የታተመውን አማራውን የትግራይ ብሄረተኞች እንዴት እንደሚጠሉት የጻፈውን ጭምር በማስረጃ አቅርባ በስጦታ መልክ አበርክታለች። ይሄውም በዚህ መልክ ለእነ ኮሀን ስለ አማራው ብሄር ማጥፋት ዘመቻ መጨፍጨፍ እና መሬቱን እና የግል ንብረቱን ጭምር በመቀማት ማባረር ገለፃ ሲደረግ የመጀመርያው መሆኑ ነው።

ቀጥሎም ስለ ኦሮሞው ፣ ጋምቤላ፣ የኢትዮጵያ ሱማሌን አስመልክቶ በሕዝቡ ላይ የሚደርሰውን የእርስ በእርስ ግጭት ቅስቀሳ እና የሚደርስበትን ግፍ ሰፊ መረጃዎችን አቅርለባች።

በየሐረርወርቅ ከቀረበው አጀንዳ ውጪ በአምባሳደር ኮሀን የቀረቡላት ሃሳቦችም ነበሩ። ዝርዝሩን በቅርብ በተከታታይ እስክናወጣ

ከአክብሮት ጋር ለዛሬ ከዚህ በላይ ባስቀመጥነው መግለጫ እንሰናበታለን።
እዝራ ካሳ
ምክትል ሊቀመንበር።
ezrakassa@gmail.com
ድል ለኢትዮጵያ!