ማስጠንቀቂያ በተለይም ለጎንደር #አማራ_ገበሬ

Print Friendly, PDF & Email

(አያሌው መንበር)

በመተማ የሱዳን ድንበር በኩል ሱዳኖች 40ኪ.ሜ ድረስ ዘልቀው ገብተው ወረራ መፈፀማቸው ታውቋል።ይህ የሆነው “የሀገሪቱ መከላከያ ሰራዊት” የአማራን ህዝብ ለማሸበር ትናንት ከድንበር ተነስቶ ወደ መሀል ሀገር በእቅድ በገባ እለት ነው።ይህ የሆነው በህወሃት ፍላጎትና የተጠና እቅድ መሆኑ ግልፅ ነው።

ስለሆነም ማንም የአማራ ገበሬ “ድንበሬ ተጣሰ” በሚል ባልተጠና ስልት የህወሃት የሴራ እቅድ ማስፈፀሚያ በመሆን ራሱን የሳት ራት አልያም የመስዋት በግ ማድረግ የለበትም። ይህ ጉዳይ የሁለት ሀገራት ጉዳይ ነው። የሚፈታውም በሀገር ዲፕሎማሲ እንጅ የአማራን ገበሬ ለመደራደሪያ በፍሪዳነት በማቅረብ መሆን የለበትም።

እናም ጊዜው የእናንተን የመጨረሻ ተሳትፎ የሚጠይቅበት ወቅት እስኪመጣ ድረስ ከህወሃት ወታደሮች (ማለትም በመታወቂያ የሱዳን ከሆኑት) ጋር አላግባብ ጦርነት ውስጥ መግባት አዋጭ አይመስለኝምና መታገስና የአማራን ህዝብ የተጠና፣አዋጭና የመጨረሻ ጥሪ መጠበቅ የተሻለ ይመስለኛል። 100 የሱዳንን ወታደር አንድ የአማራ #ሳሉግ እንደሚያነጥፈው እሙን ነው። ዲፕሎማሲያዊ ሁናቴዎች ተሞክረው የህወሃት ውስጣዊ ሴራ በአደባባይ ተነግሮ የአማራ ብሄራዊ ጥሪ እስኪካሄድ መጠበቅ ጥሩ ነው።

((ህወሃት ሰሞኑን የማትመዘው ነገር ካርድ አይኖርም። ብዙ ያልተጠበቁ ነገሮችን በደህንነቷ በኩል በሀገር ውስጥም በውጭም ልትፈፅም ትችላለች። ትኩረታችን ወልድያ ወለድ የአማራነክ ጉዳዮች ላይ ሁኖ ቢቆይ ግን መልካም ነው።አሸናፊነታች ለሁሉም ማድረስ።ዝቅተኝነት ስሜታቸውን እና ሴረኝነታቸውን ለመላ ኢትዮጵያውያን ማሳወቅ።))