መቀሌ -ወልዲያ ከተሞች (ሙሉቀን ተስፋው)

Print Friendly, PDF & Email

 

1. በመቀሌ ከተማ የነበረው አመጽ ዐማራ ፍለጋን ነበር፤ ሌሊት በባውዛ ቀንም በብርሃን ዐማራ ፈለጉ። የዐማራ የሆነ ነገር ጠፋ። በአባት ወይም በእናታቸው ዐማራ የሆኑ ዜጎች ሁሉ ራሳቸውን ለማዳን ተደብቀዋል።

በመቀሌ ጎዳናዎች አ.ማ. (አማራ) የሚል ታርጋ ያላቸው መኪናዎች ተፈልገው ታጡ፤ ከዚያ አአ የሚል ታርጋ ያላቸው የእነርሱው ቱጃሮች የሚይዟቸውን መኪናዎች ጠረማመሷቸው። አንዳንድ የግል ባንኮች ዐማራዊ ወይም ደግሞ ኢትዮጵያዊ ሀብት ናቸው በሚል ተደበደቡ፤ የሚገርመው ግን ከዚህ ድብደባ የሥርዓቱ ደጋፊ ባንኮች (ለምሳሌ ዳሸን) ጪምር ተጠቂ መሆኑ ነው።

ወልዲያ

የመቀሌ ዩንቨርሲቲ ተማሪዎች ወደ ውጭ መውጣት አይችሉም። ግቢ ተዘግተው ነው ያሉት።
**********

2. በወልዲያ የነበረውን ፍትሐዊ ሕዝባዊ ተቃውሞ ተላላኪው አቶ ንጉሡ ጥላሁን ‹‹ዝርፊያ›› ማለቱን ተከትሎ አንዳንድ የሕወሓት ሰዎች አራግበውታል። የወልዲያ ወጣቶች በትክክል ለሌለውም የዐማራ አካባቢ ትምህርት የሚሆን ነገር ፈጽመዋል። መጀመሪያ ታገሱ ከዚያም ክብራቸውን ለማስጠበቅ የሚገባቸውን ቅጣት መስጠት ነበረባቸው።

ወጣቶች የሥርዓቱ ደጋፊ የሆኑ ሰዎችንና ድርጅቶችን ማጥቃት ቢቻል ግን (በተለይ በሥራ ቀን ቢሆን ይጠቅማል) ፍትሐዊ የሀብት ክፍፍል እንጅ ወንጀል አይሆንም። ይህ በደሴም፣ በኮምቦልቻም፣ በጎንደርም ቢሆን የሚበረታታ ተግባር ነው። ከፊት ለፊት የሚገድሉን ሰዎች (በዘረፋና በሙስና የተገኘ) ፀጋ ተከምሮ ሌላው የሚራብበት ሥርዓት ማብቃት የሚችለው በዚህ መንገድ ብቻ ነው።
**********

3. ዛሬ የወልዲያ ከተማ ትግርኛ ብቻ በሚናገሩ ወታደሮች ተጥለቅልቃለች። እነዚሁ የሥርዓቱ ደጋፊ የሆኑ ሰዎች በግል የተጣሏቸውን ሰዎች ሁሉ እያስለቀሙ ነው። ይህ ሁሉ ነገር የበለጠ ነገሮችን ከማወሳሰብ የዘለለ ጥቅም እንደሌለው አቶ ንጉሡ ለአለቆቻቸው ቢነግሯቸው መልካም ነው።

 

*************

(ልሣነ ዐማራ- Amhara Press )

#ወልዲያ_እንዴት_አመሸች???

የወልዲያ ከተማ ምሽቱንም የሀዘንና የውጥረት ድባብ እንዳጠላባት ነች። በህዝቡ ውስጥ እልህ ፣ ቁጭትና አልደፈር ባይ ስሜት ይነበባል። የአጋዚ ቅልብ ጦር አሁንም በግዳጅ ላይ ነው። የከተማዋ የብአዴን ካድሬዎች ማምሻውን በስብሰባ ጥሪ ተጠምደው አምሽተዋል።

ነገ በ26/03/2010 ዓ.ም በሁሉም ቀበሌዎች አስገዳጅ ስብሰባ ተጠርቷል። የድርጅት አባላትን መሠረት ባደረገው በዚህ ስብሰባ ፤ ህዝቡን ለማረጋጋትና የወልዲያ ወጣቶች ላይ የጥፋተኝነት ታፔላ በመለጠፍ ፤ ለአመፁ መንስኤ ናቸው ያሏቸውን ወጣቶች ለማሰር የተወጠነ ውጥን እንደሆነ ውስጥ አዋቂዎች ማምሻውን ለልሳነ ዐማራ ገልፀዋል።

የወልዲያ የጎበዝ አለቆች በበኩላቸው ፤ በነገው የብአዴን ስብሰባ ሁሉም የከተማው ነዋሪ በነቂስ ወጥቶ ፤ << ብአዴን አማራን አይወክልም ፤ እስከመቼ አማራው እየደረሰበት ያለው ግፍና መከራ ይቀጥላል? ፤ ለሰላማዊ ተቋውሟችን እስከመቼ ግድያና ድብደባ መልስ ይሆናል ? ፤ የተቃጣብንን የማንነት ማጥፋትና የጭቆና ዘመቻ የምንመልሰው እኛ እንጂ ብአዴን አይደለም … ወዘተ >> በማለት ተቃውሞውን እንዲገልፅ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በተያያዘ ዜና አሁን ከመሸ ” በከተማው የውሀ ታንከር ላይ አደገኛ ኬሚካል ተጨምሯል።” የሚል ወሬ በመስፋፋቱ ህዝቡ ለተጨማሪ ጭንቀት መዳረጉን ከስፍራው የተላከ መረጃ ያመለክታል። በመሆኑም የሚመለከታችሁ የመንግስት ተወካዮች ይህ አይነቱ ስጋት ፈጣሪ ወሬ ያለውን እውነታነት ወይም ሀሠት መሆኑን በመረጃ በማስደገፍ ለህዝቡ ጭንቀት ምላሽ እንድትሠጡ እየጠየቅን ሁኔታዎች በይፋ እስኪታወቁ ድረስ ህብረተሠቡ የራሱን የጥንቃቄ እርምጃ እንዲወስድ የልሳነ አማራ ዝግጅት ክፍል ያሳስባል።

ወልዲያ