የጎንደር ዩኒቨርስቲ የሰራው ማሽን የተሳካ የእንቦጭ አረም ነቀላ አደረገ

Print Friendly, PDF & Email

ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ የሆነበት የእንቦጭ አረም ማሽን በይፋ ተመርቆ የሙከራ ስራ ጀመረ፡፡ በሰዓት 50 ኩንታል የእንቦጭ አረም መሰብሰብ ይችላል፡፡

ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ የሆነበት በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የተሰራው የእንቦጭ ማረሚያ ማሽን በይፋ ተመርቆ ዛሬ የሙከራ ስራውን ጀምሯል፡፡

ለረዥም ጊዜ ሲጠበቅ የነበረው በዩኒቨርሲቲው የተሰራው ይህ ማሽን ዛሬ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች አማካኝነት የሙከራ ስራውን በይፋ ጀምሯል፡፡

ማሽኑ በሰዓት 50 ኩንታል እንቦጭ አረም መሰብሰብ ይችላል፡፡ዩኒቨርሲቲው የተሰራው ማሽን የሰው ሀይልን ሳይጨምር እስካሁን 2.2 ሚሊዮን ብር ወጭ ተደርጎበታል፡፡

በሙከራ የተስተዋለው የፍጥነትና የመሰብሰብ አቅም ውስንነት ተስተካክሎ በሳምንቱ መጨረሻ ሙሉ በሙሉ ወደ ስራ እንደሚገባ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ኢንዳስትሪ ትስስርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን መስፍን ገልጸዋል፡፡

ማሽኑን በይፋ መርቀው ያስጀመሩት የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ደሳለኝ መንገሻ ማሽኑ እዚህ ደረጃ እንዲደርስ ከፍተኛ ጥረት እንደተደረገ ገልጸው፤ በቀጣይም ዩኒቨርሲቲው ቀሪ ስራዎቹን እንዲጠናቀቁ ድጋፉን ይቀጥላል ብለዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በእንቦጭ አረም ላይ የሚሰራቸው የላብራቶሪ ምርምር ስራዎች ተስፋ ሰጭ ውጤት እየታየባቸው መሆኑን የገለጹት ዶክተር ደሳለኝ በዘርፉ ጣናን የማዳን ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

በሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ የእንቦጭ አረም ማሽን ተሰርቶ ለሙከራ በቅረቡ መደሰታቸውን የገለጹት የአማራ ክልል ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንፎርሜሽን ኮምንኬሽን ኮሚሽነር ዶክተር ሰብስበው አጥቃው ለስራው ስኬት ቢሯቸው ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታውቀዋል፡፡

 

በጎንደር ዮንቨርስቲ የተሰራው የእምቦጭ አረም ማስወገጃ ማሽን

 
 

በጎንደር ዮንቨርስቲ የተሰራው የእምቦጭ አረም ማስወገጃ ማሽን

 
 

በጎንደር ዮንቨርስቲ የተሰራው የእምቦጭ አረም ማስወገጃ ማሽን

 
 

በጎንደር ዮንቨርስቲ የተሰራው የእምቦጭ አረም ማስወገጃ ማሽን

 
 

በጎንደር ዮንቨርስቲ የተሰራው የእምቦጭ አረም ማስወገጃ ማሽን