የመቀሌ ዮንቨርስቲ አስተማሪ ዶ/ር ኃይሌ ሙሉቀን ብአዴን አማራን እድገት በድገት እያንበሸበሸው ነው ይለናል!

Print Friendly, PDF & Email

ዶ/ር ኃይሌ ሙሉቀን በምራብ ጎጃም የአገዋዊ ዞን ዋና ከተማ በሆነችው በዳንግላ እስከ 12ኛ ክፍል እንዲሁም በአዲስ አበባ ዮንቨርስቲ በታሪክ እስክ ዶክትሬት ዲግሪ የተማረ መሆኑን የግል ትምህርት ታሪኩ (CV) ያስረዳል።

ዶ/ር ኃይሌ ሙሉቀን – መቀሌ ዮንቨርስቲ

ዶ/ር ኃይሌ እ.ኤ.አ. ከ2003 ጀምሮ በመቀሌ ዮኒቨርስቲ ተቀጥሮ እየሰራ ይገኛል። ምናልባትም የትግራይ ወያኔ ዶ/ር ሃይሌን የአማራን ህዝብ ፈጽሞ ከምድረ ገጽ ለማጥፋት ባለው ጠንካራ እቅድ መሰረት ዶ/ር ሃይሌን መቀሌ ወስዶ አማራን የማጥፋት የፖለቲካ ስልጠና እየሰጠችው ይሆናል። የትግራይ ወያኔ የቅማንት ተወላጅ ነን የሚሉትን በመቀሌ ዮኒቨርስቲ በመምህርነት ስም ቀጥሮ፣ ቢሮና እና ከፍተኛ በጀት በመመደብና በቅማንት ስም ጎንደርን ለመከፋፋል እየሰራ እንዳለው ሁሉ በተመሳሳይ መልኩ እነ ዶ/ር ሃይሌን በመቀሌ ዮኒቨርስቲ አስገብቶ አማራን የማዳከምና የማጥፋት የፕለቲካ ስልጠና እየሰጠውና በአገው ስም ጎጃምን ለመከፋፍል እየሰራ እንደሆነ ለማወቅ ይቻላል።

ለማንኛው ዶ/ር ኃይሌ ሙሉቀን አማርኛ ተናጋሪ የህወሃት ክንፍ የሆነውና የአማራን ህዝብ እጅና እግሩን አስሮ በትግራይ ነጻ አውጭ ድርጅት እያስገዛ ያለውን ብአዴንን ለአማራ ህዝብ አመጣ ያለውን እድገትና ብልጽግና እንዲሁም ብአዴንን ያደነቀበትን ጽሁፍ ከዚህ በታች አንብቡ። (ANDM turns 37 – A look at its achievements, challenges and future prospects pdf)