ማስጠንቀቅያ ለራያ ቢራ አክስዮን ማኅበር! -ከመቐለ

Print Friendly, PDF & Email

ማስጠንቀቅያ ለራያ ቢራ አክስዮን ማኅበር !

የራያ ቢራ የፖለቲካ መሣርያ ሆኖ እየሠራ ይገኛል። የትግራይን ህዝብ ለመከፋፈል ሆን ብሎ ለተነሣ የነስብሃት ነጋ ዓላማ ለማሳካት ውራይና መጽሔት የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ እንዲታተም እያደረገ ይገኛል። ውራይና የነስብሃት ነጋ እኩይ ፀረ የትግራይ ህዝብ ሤራ ቀንዯኛ መሣርያ ሆኖ ይገኛል።

የነስብሃት ነጋ ዕቅድ የትግራይ ህዝብና ትግርኛ ተናጋሪ የኤርትራ ህዝብ አስተባብሮ ትግራይ ትግርኝ የምትባል ሀገር ለመመስረት ሌት ተቀን እየተንቀሳቀሱ ይገኛለ። ይህ ዓላማ የ1968 ዓ/ም የነበረ ዓላማ ነው። በዚያን ጊዜ ያልተሳካ ዓላማ አሁን የተመቸ ጊዜ አለ ብለዉ በመንቀሳቀስ ላይ ናቸው።

የዚህ እኩይ ዓላማ እንደ ሚድያ ሆኖ እያገለገላቸው የሚገኝ ደግሞ ውራይና ተብሎ የሚታወቅ በትግርኛ የሚታተም መጽሔት ነው። ሆኖም ራያ ቢራ ከዚህ እኩይ ሥራ መውጣት አለበት። እንደ ሌሎች መጠጦች ዳሽን፣ ዋልያ፣ ሜታ በንግድ ብቻ መሰማራት አለበት። አለበለዝያ
የትግራይን ህዝብ ማዋረድ ዋጋው መክፈል አይችልም።
ዋእ ! ወዮልህ !

ከ ሙለእ ዓለም መቐለ