“በአማራነታችን እንሞታለን፣ አማራነታን አትፍቁትም” – በእስር ላይ የሚገኙ የወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄ አስተባባሪዎች

Print Friendly, PDF & Email

(አያሌ መንበር)

አማራ ነን በማለታቸው ብቻ “ወንጀለኛ” ተብለው ተከሰው እየተሰቃዩ የሚገኙትን የወልቃይት የአማራ ብሄርተኝነት የማንነት ጥያቄ አስተባባሪዎች የክስ ሂደትን ለመመልከት የሄደው ወጣት የእነርሱን ንግግር በማስቀደም እና ፎቶዎችንም በማያየዝ የላከልኝ መልዕክት ነው። ወንድሜ እንዲህ ሲል ይጀምራል፦

“ዛሬ ለመጀመሪያ ጊዜ የልደታ 4ኛ ችሎት ላይ ታድሜ ነበር። በጣም የሚያቆስል ነገር ተመልክቸ መጣው በአማራነታችን እንሞታለን.. አማራነታችን አትፍቁትም.. ዘራይ ሊበቀለን ነው የመጣው.. ያሥሥለቅሳል።

#ብልቱን ቆርጠውታል አንዱን (ማስረሸን ማለቱ ነው)). ውይይ በጣም ያማል። አማራው አሁንም መንቃት አለበት ጽንፈኛ ብሄርተኝነቱን አፋፍሙት እግዚአብሄር ይርዳን።”

እና ምን ለማለት ነው በደላችን በጨመሩት ቁጥር እኛ ብሄርተኝነታችን እያጠበቅን፤ ከእነርሱ ጋር ሊያገናኙን የሚችሉትን ሁሉ እየበጠስን ለመሄድ ያግዘናል።

በአዲስ አበባ በእስር ቤት የሚገኙ የወልቃይት አማራ ማንነንት የኮሚቴ አባላት እና የዋልድባ ገዳም መነኮሳት

**********

(ሙሉቀን ተስፋ እንደጻፈው)

የዛሬው የትግሬዎች “ዳኝነት” የመጨረሻው ማጠቃለያ

አስቻለሁ ደሴ በመጀመሪያ ዳኞቹን አስፈቅዶ የደረሰበትን ስቃይ ሱሪውን አውልቆ ለማሳየት ሲሞክር እነዘርአይ ከለከሉት። ሱሪውን አውልቆ “የኢትዮጵያ ሕዝብ ይፍረደኝ” አለ። ዳኞች ተናደዱ፤ ያናደዳቸው የእነርሱ ወንድሞች በጨለማ የደበደቡትን በአደባባይ ለምን ተናገርክ በማለታቸው ነው። በተከሳሾች ተቃውሞ የተቋረጠው ችሎት መልሶ ሲጀመር ችሎት በመድፈር ከሦስት እስከ 6 ወር እስር እኚሁ ዳኞች ፈረዱ፤ ጊዜ የሰጠው ቅል ድንጋይ ይሰብራል እንደሚባለው።

ታዲያ በችሎት መድፈር ከተፈረደባቸው የመጀመሪያው ነጋ ዘላለም ነው ሙሉ ሰሙ። “ባይገባችሁ ነው እንጂ እናንተም ይህን ወንበር ያገኛችሁት በዐማራው ደም ነው” ሲላቸው ነው የፈረዱበት። በጠቅላላ አራት ተከሣሾች ላይ ነው ተጨማሪ እስር የበየኑት።

ከአራቱ አንደኛው 3 ወር የተፈረደበት ልጅ “እነሱ ተፈርዶባቸው እኔ አልቀመጥም” በማለቱና ከወንድሞቹ ጋር በመቆሙ ነው የተበየነበት። እንዲህ ያለ ዐማራዊ ወንድማማችነት ማደግ አለበት።

ዳኞቹ ግን፤

የዳኛ መዳቢው በሪሁን የተባለው ትግሬ ዛሬ ሳጣራ ስድስት ኪሎ መመረቅ አቅቶት እንደተባረረ ነው የእሱ ባቾች የሚያውቁት።

ዘርአይ ወልደሰንበት ደግሞ የዐማራ በቀል ስሜቱ እንዳለ ሆኖ የተዘፈቀበትን የሙስና ወንጀል ፖለቲካዊ ቅርጽ ለማስያዝ እንደሚሞክር ፍትኅ ሚኒስቴር የሚሠሩ ሰዎች ተናግረዋል።

ፍርዱን ከሰጡ በኋላ በእብሪት ‹‹በሕግ›› ጥላ ሥር ያሉ ዐማሮችን ሞራላቸውን ለመንካት ያደረጉት ጥረት እጅግ የሚገርም እብሪት ሆኖ ተመዝግቧል።