ትችቴ “ለቤተ አማራ ወኪል” በጀርምን የአማራ ማሕበር ሕዝባዊ ስብሰባ ስለአደረገው የመገንጠል ቅስቀሳ

Print Friendly, PDF & Email

ጌታቸው ረዳ (ኢትዮፕያን ሰማይ)

ተከታታዮቼ ሰላም እንደምን ሰነበታችሁ። ወደ ርዕሴ ከመግባቴ በፊት እንደተለመደው አንድ ሁለት ነገር ማለት እፈልጋለሁ። መጀመሪያ በርካታ ወንድሞች እና እህቶች ዛሬም ያለማቋረጥ ስለ አዲሱ መጽሐፌ አንብባችሁ ደስታችሁን ለገለጻችሁልኝ ወገኖች አመሰግናለሁ። ከነዚህ ውስጥ ወ/ሮ ጸሐይ የተባሉ እህት ከመኔሶታ ስለ ላኩልኝ የማበረታቻ እና የደስታ መግልጫ ካርድ በተመለከተ አጠፋውን አመሰግናለሁ ለማለት ፈልጌ ስልክዎን ወይንም ኢመይልዎን ስላልጻፉበት እባክዎን ስልኬን በመደወል ያነጋግሩኝ ወይንም ኢሜይል ያድርጉልኝ ፤ እጅግ እጅግ በጣም እጅግ አመሰግናለሁ። እንዲሁም ከእስራል እና ከመሳሰሉት የላካችሁልኝ ደስታ መግለጫ አመሰግናለሁ። እባካችሁ ተመልሼ የምደውልበት ወይም የማገኛችሁበት መንገድ እንዲመቸኝ ስልክ ወይንም ኢመይላችሁ ማስቀመጥ አትርሱ።

በአንድ ጉዳይ ለመተቸት ስዘጋጅ፤- አንድ ወዳጄ በኢመይል፤ “የጀርመኑ አማራ ሕብረት ስብሰባ” እንዳዳምጥና የተረፈችህን ስስ አንጀትህን ሳታቃጥል ቤተ አማራ ስለተባለው አንድ የድሮ ጦር “የሻምበል” ማዕርግ ያለው ተናጋሪ ስለ አማራን የመገንጠል ፕሮፓጋንዳውን በትዕግስት አድምጥ ብሎ በመግለጽ እዛው ውስጥም የኔን ስም አንስቶ ሲወራጭ የሰማውን ወዳጄ ልኮልኝ፤ ስለ ሌላ ጉዳይ ለመተቸት ያሰብኩትን ሃሳቤን ለውጬ በዚህ “አዲስ- የአማራ ተገንጣይና አስገንጣይ” ግለሰብና መሕበር (ቤተ አማራ) አንድ ለማለት ወሰንኩኝ።

የአማራ ማህበር በጀርመን ህዝባዊ ስብሰባ

https://youtu.be/tyLzVCfC7E4

መጀመሪያ በቀና መንፈስ ተነሳስተው ጠበቃ ላጣው የአማራው ሕዝብ ፍትህ ለማስገኘት ሲሉ የጉባኤውን አዘጋጆቹንና እና ይህች ከተናጋሪዎች መሃል ያየሁዋትን ከዚህ በታች ያለቸው ውብ ታጋይ እና ድንቅ ኢትዮጵያዊት አርበኛ ከልብ ላመሰግናት አወዳለሁ። ስሟን አላወቅኩትም፤ ግን ለማሕበርሽ እና ለአንጪው ያለኝን አክብሮትና ምስጋናየ ይድረስሽ። ስምሽን ባለማወቅየ ይቅርታ። …  (Read more pdf)