ከትግራይ ሕዝብ ዝምታ ጀርባ፣ – መቅደላ – የዐኅኢአድ ማዕከላዊ ምክር ቤት ልሣን

Print Friendly, PDF & Email

መቅደላ – የዐኅኢአድ ማዕከላዊ ምክር ቤት ልሣን
ቅጽ 01 ቁጥር 001 ቀን፦ኅዳር 6/2010 ዘወትር ኀሙስ ኀሙስ በ15ቱ ቀን የሚወጣ

ከትግራይ ሕዝብ ዝምታ ጀርባ፣

በቅርቡ የወያኔ የወግ ዕቃ የሆነው፣ጠቅላይ ሚኒስቴር ኃይለማርያም ደሣለኝ በሰጠው መግለጫ፣ የኦሮሞና የዐማራ ሕዝብ የፈጠሩትን አንድነትና ያሳዩትን ወንድማማችነት፣ በተመሳሳይ ሁኔታ በዐማራውና በትግራይ ሕዝብ መካከል እንደሚካሄድ ተናግሯል። በእርግጥ፣የትግራይ ሕዝብ በረጅም ጊዜ ታሪኩ፣ከአጎራባቹ የዐማራ ነገድ ጋር በፍቅርና በመተሳሰብ ተደጋግፎ ከመኖሩ በተጓዳኝ፣ የተጋባና የተዋለደ፣ ክርስትና ፣ እስልምና እና ይሁዲ ሃይማኖቶችን ተጋርቶ የኖረ ወድማማችና እህትማማች ሕዝብ መሆኑ ይታወቃል። በዚህም የተነሳ፣ ለትግራይ ሕዝብ ጎንደር፣ ጎጃም፣ ወሎና ሸዋ ክፍለ-ሀገሮች ቤታቸው፣ መኖሪያቸው፣ የወግ ማዕረግ ማያቸው እንደሆነ በየታላላቅ ከተሞች የሚገኙት ሆቴሎች፣ ጋራጆች፣ ሱቆች፣ ሠፋፊ እርሻዎች፣ የቤትና ቢሮ ዕቃዎች መለስተኛ ፋብሪካዎች፣ ወዘተ ባለቤቶች የነማን እንደሆኑ የምናውቀው ነው።

በታሪካችን ለሥልጣን ሲባል ከሚደረግ የሥልጣን ተሻሚዎች ፍትጊያ ውጭ፣ በረጅሙ ታሪካችን፣የዐማራና የትግራይ ሕዝብ ግንኙነት የሰምና የፈትል፣ የወተትና የውኃ ያህል ለመለየት የማይቻል፣ በልዩ ልዩ መንገዶች የተያያዘና ውሕድ አካል እንደነበር ይታወቃል። ይህን የቆየና መልካም ትስስርና ዝምድና ግን፣ከትግራይ ሕዝብ አብራክ ወጣን የሚሉን ወያኔዎች፣ ከዐማራው ላይ በተለይም በጎንደሬው ላይ የሚያሳዩት ደመኝነትና ዘር እስከ ማጥፋት የደረሰ ጥላቻ ከምን የመነጨ ነው? ብለን እንድንጠይቅ አስገድዶናል። ለጥያቄው የተለያዩ መልሶች መስጠት የሚቻል እንደሆነ ብንገነዘብም፣ ለዐማራው ጥያቄው እንቆቅልሽ ሆኖበት ለ26 ዓመታት በዝምታና በትዕግሥት ሲመለከት ቆይቷል። ነገሩን የበለጠ አጠያያቂ የሚያደርገው፣ ወያኔዎች የትግራይን ሕዝብ በውድም በግድም ዐማራውን በጠላትነት እንዲመለከተው ከማድረጋቸው በተጓዳኝ ፣በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ሌሎች ነገዶችን «ዐማራው የእኛም የእናንተም የጋራ ጠላት ነው፤ እርሱን ለማጥፋት ተባበሩን» ማለታቸውና በመላ አገሪቱ በሚኖረው ዐማራ ላይ የዘር ማጥፋትና የዘር ማጽዳት ወንጀል እንዲፈጸምበት ጃዝ ! በለው! ብለው ዘመቻ መክፈታቸው ነው። ዐማራው በጥቅሉ ትግሬንም ሆነ ሌሎች ነገዶች ላይ ምን በደለ ፈጸመ? …… (Read more, pdf)