አፓርታይድ በቤኒሻንጉል ክልል – ትግሬዎች ከ600 ሺህ ብር ጋር በአውሮፕላን ተሸኙ፣ አማራሮች ተፈናቀሉ

Print Friendly, PDF & Email

(በስዩም ተሾመ)

የቤኒሻንጉል ግሙዝ ክልል የርዕሰ መስተዳደር እና የካቢኔ ጉዳዮች ኃላፊ አቶ #ሰለሞን_ጂሬኛ አፓርታይድ በተግባር ምን እንደሚመስል እንዲህ ይነግሩሃል። “የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት #የትግራይ ክልል ተወላጆችን 600ሺህ ብር እና #የአውሮፕላን_ትኬት ሸፍኖ ልኳቸዋል”። በክልሉ የሚገኙ #የአማራ ክልል ተወላጆች በተመለከተ ደግሞ “#በሕገ_ወጥ መንገድ የያዙት መሬት እንዲለቁና ወደ መጡበት ክልል እንዱመለሱ ተደርጓል” ይሉሃል።

…አፓርታይድ በተግባር ይህን ይመስላል። “ይሄ በደቡብ አፍሪካ በነበረው የአፓርታይድ ዘመን የተፈፀመ አድልዎ ነው” አይደለም። እዚሁ በሀገራችን በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተፈፀመ ነው። “የቆየ ታሪክ ነው” እንዳትሉኝ ዘገባው የቀረበው ሕዳር 04/03/2017 ዓ.ም ነው። “ውሸት ነው!” እንዳትሉኝ ዘገባውን ያቀረበው “አዲስ ዘመን ጋዜጣ ነው!”

ይሄው ነው አማራን ገድለው ከመሬቱ አፈናቀሉት፣ የትግራይ ተወላጅን ከ600ሺህ ብር ጋር በአውሮፕላን ሸኙት። ምክንያቱም ይሄ “የብሔር አፓርታይድ” ነው።