የአዴሃን ወታደራዊ ሃይል በመተማ ኮርጃሙስ ላይ ይንቀሳቀስ በነበረው የወያኔ ሰራዊት ላይ ጥቃት ሰነዘረ

Print Friendly, PDF & Email

የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ (አዴሃን) ወታደራዊ ሃይል በመተማ ኮርጃሙስ ላይ ይንቀሳቀስ በነበረው የወያኔ ሰራዊት ላይ ጥቃት ሰነዘረ፡፡ አዴሃን በወያኔ ሰራዊት ላይ ጥቃቱን የፈጸመው ጥቅምት 29 ቀን 2010 ዓ.ም ከሌሊቱ 7:00 ሰዓት ላይ ሲሆን በዚሁ በመተማ ኮርጃሙስ አካባቢ በተደረገው ዉጊያ ከወያኔ ሰራዊት 3 ሙት እና 9 ቁስለኛ ሲሆኑ ከአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ ደግሞ አንድ ታጋይ ተሰውቷል፡፡ የአዴሃን ወታደራዊ ሃይል ጥቃቱን ካደረሰ በኋላ በሰላም ወደ ቦታው የተመለሰ ሲሆን ጥቃቱን ከፈፀመው የአዴሃን ወታደራዊ ቡድን መሪ ጋር ቃለ ምልልስ በማድረግ በቅርብ ቀን ዝርዝሩን የምናቀርብ መሆኑን እንገልጻለን፡፡ ዝርዝር ዘገባውን ከዚህ ላይ ያዳምጡ