የዐማራ ኅልውና ለኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (ዐ.ኅ.ኢ.አ.ድ.) ፕሮግራም

Print Friendly, PDF & Email

የዐማራ ኅልውና ለኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት መርሓግብር

መጋቢት 2009 ዓ.ም.

ክፍል አንድ፦

መግቢያ

ኢትዮጵያ ጥንታዊ ከሚባሉትና የራሳቸውን የፀና መንግሥት መሥርተው በሕዝብ አስተዳደርና በሥልጣኔ ቀደምት ከነበሩት ሀገሮች አንዷ እንደሆነች የዓለም ታሪክ ያረጋገጠው ዕውነታ ነው። ምንም እንኳ የመልክዓምድር ክልሏ በተለያዩ ጊዜአት ሲሰፋና ሲጠብ የነበረ ቢሆንም፣ ከሦስት ሺህ ዘመን በላይ የታወቀ ክልል እና የፀና መንግሥት የነበራትና ለሌላው ዓለም ሊተላለፍ የቻለ የሥልጣኔ ምንጭ ሀገር እንደሆነች ታሪክ እና የሥነ ምድር-ቅሬተ አካል የምርምር ውጤቶች ያሳያሉ። በኢትዮጵያ ረጅም የታሪክ ዘመን፣ በሁሉም የኢትዮጵያ ሥርዓተ መንግሥታት ውስጥ በአስተዳደር፤ በሥልጣንና በሥራ ድርሻ ክፍፍል ላይ እንደወቅቱ ነባራዊ ሁኔታ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ነገድና ጎሳ የተካፈሉበት እንደነበር የአገሪቱ አንድነት ለረጅም ዘመን ፀንቶ መዝለቁ ሕያው ምሥክር ነው።
ከሁሉም በላይ፣ የኢትዮጵያ አንድነት፣ ነፃነት፣ ሉዓላዊነትና ብሔራዊ ጥቅም ተጠብቆ እንዲዘልቅ፣ በአራቱም የአገሪቱ ማዕዘኖች የክብር ዘብ ሆነው ከኖሩት የኢትዮጵያ ነባር ነገዶችና ጎሳዎች መካከል፣ ዐማራው አንዱና ግንባር ቀደሙ እንደሆነ ማንም ይስተዋል የሚባል አይደለም። በመሆኑም ዐማራው በኢትዮጵያ ረጅም ታሪክ ውስጥ በሁሉም መስኮች፣ ማለትም፦ በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ፣ በማኅበራዊ ኑሮ እና በአገር መከላከያ የበኩሉን የጎላ አስተዋጽኦ አድርጓል። ሀገሪቱን ከውጭ ከሚመጡ ወራሪዎች ለመጠበቅ ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ነገዶችና ጎሳዎች ጋር በመሆን ከፍተኛውን ድርሻ በመያዝ የሕይዎት፣ የአካል እና የገንዘብ መስዋዕትነት ከፍሏል። ይህም በመሆኑ፣ ዐማራው ከኢትዮጵያዊነት ጋር የአንድ ሣንቲም ሁለት ገጽታዎች የሆነ ማንነትን የገነባ ሕዝብ ለመሆን የበቃ ነው። ዐማራው በአሰፋፈር ረገድ በግራኝ እና በኦሮሞ የተራዘመ ወረራ ምክንያት፣ ከምሥራቅ፣ ከደቡብ ምዕራብና ከደቡብ ኢትዮጵያ ተገፍቶና ማንነቱን ተነጥቆ፣ በመሀል፣ በሰሜንና በሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ በብዛት እንዲኖር ቢገደድም፣ በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍሎች (ጠቅላይ ግዛቶች) በከፍተኛ ደረጃ ተሰራጭቶ የሚገኝ ታላቅ ሕዝብ ነው። ለወደፊቱም ኅልውናውን አስከብሮ፣ ኢትዮጵያዊነቱን ለድርድር ሳያቀርብ፣ በማንነቱ ፀንቶ የሚኖር ሕዝብ ነው።

ይኸም ሆኖ፣ ዐማራው በኢትዮጵያ በነበሩት የአገዛዝ ሥርዓቶች ሁሉ፣ በሌሎቹ ኢትዮጵያውያን ላይ የደረሱና የተፈፀሙ ጭቆናዎችንና ግፎችን እንደ ሕዝብ አብሮ ሲቀበል ኖሯል። ስለዚህ ሮማን ፕሮቻስካ፣ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነትን ለማጥፋት በሰበከው ፀረ-ዐማራና ፀረ-ኢትዮጵያ ፕሮፓጋንዳ የተለከፈው የግራው የዓለም አመለካከት ትውልድ እንዳራመደው ሳይሆን፣ ከሌሎች ተነጥሎ ተጠቃሚም፣ ገዥም እንዳልነበር የሚገኝበት ነባራዊ ሁኔታ አስረጅ ነው። ስለሆነም፣ የዐማራው ነገድ በተለያየ ጊዜ በነበሩ የአገዛዝ ሥርዓቶች፣ እንደማናቸውም የኢትዮጵያ ነገዶችና ጎሳዎች «ነበሩ» የተባሉትን ጭቆናዎችና ግፎች ተቀብሏል። ይልቁንስ ጨቋኝና አፋኝ አገዛዞችን ለማስወገድም በተደረጉ ሕዝባዊና ቡድናዊ እንቅስቃሴዎች ግንባር ቀደም በመሆን ታግሏል፣ መስዋዕትነትም ከፍሏል። ለአብነት ያህል በዐፄ ኃይለሥላሴ የአገዛዝ ዘመን የነደጃዝማች ታከለ ወልደሐዋርያት እና የእነ ጄኔራል መንግሥቱ ንዋይ ያልተሳኩ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራዎችና በኢትዮጵያ ተማሪዎች እንቅስቃሴ የዐማራው ነገድ ልጆች የግንባር ቀደምትነቱን ሚና መጫዎታቸው የሚዘነጋ አይደለም። ……  (Read more, pdf)