በሰሜን ሸዋ በምንጃር ሸንኮራ ህዝቡ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ አደረግ

Print Friendly, PDF & Email

የምንጃር ሸንኮራ ህዝብ በፌድራል መንግስቱም ሆነ በክልሉ የአማራ መንግስት ምንም አይነት የኢኮኖሚና የማህበራዊ አግልግሎት እየተደረግን አይደለም ብለዋል። የምጃር ሸንኮራ ህዝብ በርካታ የአስተዳድር፣ የማህበራዊና የኢኮኖም ችግሮችና በደሎች እየተፈጸሙበት ይገኛሉ።

በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ መብራት በተከታታይ ለ13 ቀናት ጠፍቶ በመቄየቱ ምክንያት በዛሬዉ እለት ሰላማዊ ሰልፍ ተካሂዷል። በወጣቶችና በአረርቲ ከተማ ነዋሪዎች በሰላማዊ ሰልፉ ላይ በዋናነት ሲቀርቡ የነበሩ ጥያቄዎች፦

1. ለመብራት ችግር ዘለቄታዊ መፍትሄ ይሰጠን
2. የዘይትና የስኳር ሰልፍ ይቅር
3. ፍትሃዊ የሆነ የግብር አከፋፈል ስርዓት ይዘርጋ
4. ለኢንዱስትሪ ፓርክ የእርሻ መሬት ለሰጡ አርሶ አደሮች የተከፈለዉ ካሳ በቂ እና ፍትሃዊ አይደለም
5. ለወጣቶች የሚፈጠረዉ የስራ እድል በቂ አይደለም፤ ለወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ የተመደበዉ ተዘዋዋሪ ፈንድ ወጣቶችን ተጠቃሚ አድረጎ አላየንም እና ሌሎችም ጥያቄዎች ተነስተዋል።

የምንጃር ሸንኮራ ህዝብ ያደረገውን የተቃሞ ሰልፍ ተከትሎ በአካባቢው የሚገኘውና ንብረትነቱ የቻይና የሆነው የችቡድ ፋብሪካ እንዲቃጠል ተደርጓል። የአካባቢውን ደን እያወደመው ነው በሚል ተቃውሞን የሚያሰማው የምንጃር ሕዝብ ሸንኮራ ላይ ያለው የችቡድ ፋብሪካ እየተቃጠለ እንደሆነ መረጃዎች ደርሰዋል።

በሰሜን ሸዋ ምንጃር ሸንኮራ የተደረገ ሰላማዊ ሰልፍ ጥቅምት 29 2010 ዓ.ም

በሰሜን ሸዋ ምንጃር ሸንኮራ የተደረገ ሰላማዊ ሰልፍ ጥቅምት 29 2010 ዓ.ም

በሰሜን ሸዋ ምንጃር ሸንኮራ የተደረገ ሰላማዊ ሰልፍ ጥቅምት 29 2010 ዓ.ም