ፕ/ር መስፍን ወያኔዎች ስልጣን በፈቃዳቸው እንዲለቁ ከገደሉት ወንጀልና ከዘረፉት ንብረት ጋር በነጻ ይሂዱ ይላሉ

Print Friendly, PDF & Email

ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም November 4 2017 በፌስቡክ የጻፉትን ከዚህ በታች ያንብቡ።

*********

ለፌስቡክ ፈላፋስዎችና በራሳቸው ፈቃድ የጎሣ አለቆች ለሆኑ ጥያቄዎች ላቅርብ፡—

1. ወያኔ በፈቃዱ ሥልጣኑን ቢለቅ በሥልጣን ላይ ሆኖ ለፈጸመው ብልግና ሁሉ ለፍርድ ይቀርባል ወይ?

2. ወያኔ በፈቃዱ ከሥልጣን ቢወርድ በአገር ውስጥ ያጋበሰውን ሀብት ሁሉ ይነጠቃል ወይ?

3. በውጭ አገር ያሸሸውን ሀብትስ ይከሰስበታል ወይ?

እነዚህን ጥያቄዎች በአዎንታ መመለስ ወያኔ በፈቃዱ ከሥልጣን እንዳይወርድ ማረጋገጥ ይመስለኛል፤ ጥያቄዎቹን በሌላ በኩል ስናያቸው በአንድ በኩል ኢትዮጵያ እንደአገር እንድትቀጥል ከተፈለገና የኢትዮጵያ ሕዝብም አዲስ ሥርዓትን አንዲገነባ ሁኔታዎችን ለማመቻቸት ከተፈለገ ይህንን የኢትዮጵያን ህልውና ያዘለ ጉዳይ ለወያኔ ምሕረት ማድረግና የያዘውን ሀብት እንደያዘ እንዲቀር ከማድረግ ጋር ሚዛን ላይ ማስቀመጥ አለብን፤ የትኛው ያመዝንባችኋል? ቂምና በቀል፣ ሀብት? ወይስ ይቅር ለእግዚአብሔርና ሀብቱን መተው?

***