በሚስጥር ስምምነት የበረከት ስምዖን ስራ መልቀቅ እና የ TPLF ብልጣብልጥ ቀጣዩ ድራማ!

Print Friendly, PDF & Email

(ከአዳነ አጣናው)

መለስ ዜናዊን በመንፈስ ቅሪተ-አካልነት ወክሎ የሚንቀሳቀሰው በረከት ሰሞዖን ስሞኑን ስራ ለቋል። ሆኖም ግን የስራ መልቀቂያ ያቀረበው በግፊት አና በትጽእኖ ሳይሆን ቀድም ሲል በወያኔ አመራር በተደረሰ ስምምነት መሰረት ነው። በወያኔ አጠራር “መሰረታዊ ለውጥ” (Far Reaching Change) ) ለማምጣት የወያኔው አመራር በረከትን ጨምሮ በተስማሙት መሰረት ስራ መልቀቁ የግድ ነው። ገና ብዙዎቹ ስራ ይለቃሉ። ይህ የስራ መልቀቅ ሀይለማሪያምን ሊጨምር ይችላል። ግን በዋናነት መታወቅ ያለበት ወያኔ ያዋጣኛል ብሎ በተለመው መሰረት የወያኔ ቁንጮ ባለስልጣናት እንዲለቁ መደረጉን መዘንጋት አይገባም። ወያኔ በተለመው መሰረት የሚካሄድ የስራ መልቀቅ ሂደት ነው።

አሁን መሬት ላይ ያለው ሁኔታ ለወያኔ ትልቅ ችግር የሆነው ትላንት ተንቆ የነበረው ዛሬ ተጠናክሮ ብቅ ያለው ኦፒዲኦ/OPDO ነው። ኦፒዲኦ የርእሰ መንግስትነቱን ቦታ ይፈልጋል። ይህንም ጉዳይ ለወያኔዎች እና ጭፍሮቻቸው ተነግሯቸዋል። ወያኔ ሀሳቡን በቀጥታ ባይቃወመውም በጥያቄው ላይ መደራርደር ይፈልጋል። በድርድሩ ከተስማሙ ወያኔ ኦፒዲኦ መራሂ-መንግስትነቱን ቢረከብ አና በተወሰነ ደረጃ ወያኔ ከኋላ ሁኖ ቁልፍ በሆኑ ጉዳዮች ላይ የሚዘውርበት መንገድ በስምምነቱ ከተካተተ ኦፒዲኦ የጠቅላይ ሚንስትርነቱን ቦታ እንዲያገኝ ያደርጋል። አንዳንድ የኦሮሞ ተወናዋኞች ደግሞ ወያኔ ከኋላ ሁኖ የሚዘውረው ስምምነት ለማድረግ ፈቃደኝ አይደሉም።

ሌላው ብኣዴን አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ እወክለውአለሁ የሚለውን ህዝብ በስሩ ማሰባሰብ የሚችል አውራ-መሪ የለውም። ሁሉም አመራሮቹ በጥንቃቄ በበረከት ደካማ መሆናቸው ተረጋግጦ የተሾሙ ናቸው። ይህ የተደረገበት ምክንያትም ሆን ተብሎ በበረከት እና በወያኔ መሪዎች በቀመሩት ስሌት መሰረት ነው።
ከአንድ አመት በፊት ብኣዴን በበረከት ድጋፍ ወደ ህዝብ ቀርቦ የህዝብ ብሶትን ማዳመጥ ጀምሮ ነበር። በዚህ ወቅት ገዱ በበረከት ትእዛዝ ህዝብ የሚጠይቃቸውን ጥያቄዎች በማቀንቀን የህዝብን ድጋፍ ከሀገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን ከውጭም ጭምር ማሰባሰብ ችሎ ነበር።

በረከት አሁን ሌላ የፖለቲካ ቆብ ጭኗል። እንደአለፈው አመት የህዝብን ጥያቄ መደገፉን አቁሟል። ገዱም ከበረከት ፍላጎት ውጭ ለማድረግ ከቶ አይቻለውም ስለሆነም አሁን ያ የህዝብ ድጋፍ የለም። ገዱን በህዝብ ይጠላ ዘንድ ወልቃይትን አልፎ ጠገዴን ከሁለት ከመክፈሉ በላይ ግጨውን ለትግራይ ተቆርሶ እንዲሰጥ ገዱ በአደባባይ እንዲፈርም ተደርጉል። ገዱም ከግጨው ፊርማ በኋላ የፖለቲካ ሞት ሞተ።እንዳይነሳ ሁኖ። አሁን ትግራይ 328 ኪሎ ሜትር እርቀት ተጉዛ ግጨው ድረስ ግዛት አግኝታለች። በረከት ሰምዖን ምስጋና ይግባው እና።

ከአሁን በፊትም መላኩ ፈንታ የህዝብ አይን መሳብ ሲጀምር በረከት ጠልፎ እስር ቤት እንደከተተው የቅርብ ትዝታ ነው። አሁን በረከት በወሰነው መስረት ጉደኛው ብኣዴን ክህወሀት ስር ከመለጠፍ ሌላ አማርጭ የለውም። ከፖለቲካው የይገባኛል ጥያቄ ወጥቶ ድሮ ወደነበረበት ህወሀትን ወደ-ማጀብ ስራው ተመልሷል። ኦፒዲኦ እና ወያኔ ከተጣሉ በሎሌነት ወያኔን ለማገለገል ድሮም የለመደው ስለሆነ የሚጎረብጠው አይደለም። እንዲያውም ወያኔ እና ኦፒዲኦ ከተጣሉ እንጀራው ከፍ ይላል። ያም ሆነ ይህ በረከት ስራ ቢለቅም የብኣዴን ፈጣሪነቱ አልተነካም።

ይህ በወያኔ ለውጥ የተባለው ነገር በዚህ ወር መጨረሻ የሚጀምር እና በቀጣዩ March የሚቋጭ ይሆናል። ይህ የእነሱ ስሌት ነው። እስከዚያ ግን ምን እንደሚመጣ መተንበይ አይቻልም። የአሜሪካን ተፅእኖን እንዲህ በቀላሉ የሚጋፉት ነገር አይደለም። አንዳንድ የምርጫ ህጎችን ሊያሻሽሉ ይችላሉ። በግልጽ እርስ በርሳቸው ለመዋጋት ተጽእኖው ቀላል አይደለም።

ይህን ካልኩ ስለ በረከት ትንሽ ልበል። እንደሚታወሰው በረከት ላይ አንዳንድ ነገሮች ማለት ከጀመርን ሳምታት አልፈዋል። ያለ ምክንያት አይደለም። በረከት ከቤተሰቦቹ ጋር በለጋ እድሜው ሲመጣ እጁን ዘርግቶ ሳይደላው ያለውን ያካፈለውን የኢትዮጵያ ህዝብ በአጠቃላይ በተለይ ደግሞ የጎንደርን ህዝብ እጅ ነክሶ ለማጥፋት ዘር ቆጥሮ ከወያኔዎች ጋር ሲያሴር ከልብ ይነዝረናል። ጆከር ሁኖ ላለፉት 27 አመታት ደባ መፈጸሙን ስናስታውስ ደግሞ እኩይነቱ በፊታችን ድቅን ይላል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ የተለያዩ ፍላጎት ያላቸውን ጸረ ኢትዮጵያ ሀይላት ጥቅም ለማስጠበቅ ሲል የሄደባቸውን የፖለቲካ ሂደት ስለምንረዳም ነው።