የማዳኛው ክኒን ኢትዮጵያዊነት ነው!

Print Friendly, PDF & Email

(ገብሬአል አዛ ተሰማ)

የእኛን መኖር ማሳወቂያውና የማዳኛው ክኒን ኢትዮጵያዊነትነው። እንደ ሰው ለተፈጠረ ህሊና ላለው ፍጡር። በዚህ የአንድነት ቡቃያዎች የፍቅር መርከብ ሁሉም መሳፈር ይኖርበታል።

የአማራና ኦሮሞ ህዝብ አንድነት ለኢትዮጵያ አንድነት ነው። ሆኖም ኢትዮጵያ ከዚህም በላይ ናት። የአፍር የትግራይ፣ የደቡብ፣ የቤኒሻንጉል፣ የጋምቤላና ወ.ዘ.ተ ህዝብ ከኢትዮጵያ ሌላ እናት የለውም። እናም የሮኦሞና የአማራ ወጣቶች ባሳዩት ፍቅር በተለይ የትግራይ ህዝብ የሚነቃበት ጊዜ አሁን መሆን አለበት።

በእኔ እምነት የትግራይ ህዝብ ወንድምና እህቶቹን የሚጠላ አይደለም። ነገር ግን የወያኔ ነገር “አማራና ኦሮሞ አብረው መቆም ከጀመሩ ያኔ ድርጅቴ ህውሀት ማቅ ትለብሳለች፣ የትግራይ ህዝብ ህልውና በአመሰራውና በኦሮሞው ፍቺ ላይ የተመሰረተ እንደሆነ ለአፍታም መዘንጋት የለበትም፣ መልሰው ጋብቻ የሚፈጥሩበት platform ካገኙ ህውሀት በይፋ ያከትምለሰታል ” መለስ ዜናዊ ከ16 አመት በፊት በትግርኛ ቋንቋ ከተናገረው። “ቅዠት” ባልጠበቀው በወያኔ ፀረአንድነት መንገድ አጣብቂኝ ውስጥ እንዲገባ ተደረገ እንጂ ስለዚህ ያለፍላጎቱ የተፈጠረበትን የአንድነት ክፍተት የሚሞላበትን ስልት ለመፈለግ ከዚህ በላይ አጋጣሚ ሊኖር አይችልም። የ100 ሚሊዮን ህዝብ ልብ ሸፍትዋል።

አያት ቅድመ አያቶቸው ደማቸውን ያፈሰሱበት፤ አጥነታቸውን የከሰከሰቡት አገር የኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን የፍቅር ልብ ለሁሉም ክፍት ነው። አማራና ኦሮሞ ዜጎች የከፈቱት የፍቅር አዳራሽ ለማንም አይጠብም።

ኢትዮጵያውያን አስተዋይ የኦሮሞና የአማራ ወጣቶች ባቀጣጠሉት የፍቅር መብራት እየተመሩ የደበዘዘ የአንድነት ታሪካቸውን ዳግመኛ ሊያደምቁት ይገባል። የኦሮሞ ወጣቶች የጀመሩት የታሪክ እርማት ስርዝ ድልዝ ባለበት ገፅ ሁሉ ለኢትዮጵያ የህልውና ተጋድሎ ወጣታዊ ተጋድሎ ሊቀጥል ይገባል የኢትዮጵያ ጉዳይ እረመጥ ነው። እናንተ የኦሮሞና የአማራ የኢትዮጵያ ወጣቶች፣ ባስተዋይ ምግባራችሁ ሁላችንም ኮርተናል፤ ኢትዮጵያም ለዘላለም ትኮራባችኋለች። አሁን ላለው ወጣት ትውልድ ብቻ ሳይሆን፤ ለጎልማሳው ትውልድም ልዩ የክብር ስጦታ ነው።

ኢትዮጵያዊነት የትናንቱን ታሪክ የሚያስቡበት ብቻ ሳይኾን ዛሬ የሚኖሩበት ነገም ተስፋ የሚያደርጉበት ሕይወት ነውና።