በጣር ላይ ያለው ጣና የይድረሱልኝ ጥሪ፣ የጣና ሀይቅና አካባቢው ደህንነት ፈንድ የባንክ ሂሳብ ቁጥር

Print Friendly, PDF & Email

የጣና ሀይቅና አካባቢው ደህንነት ፈንድ የባንክ ሂሳብ ቁጥር

ባህር ዳር፡ ጥቅምት 21/2010 ዓ/ም (አብመድ)

1000224609853 Swift code… cbetetaa

ከሰሞኑ የክልሉ ካቢኔ የጣና ደህንነት ፈንድ አቋቁሟል። የአማራ ክልል አካባቢ ደን እና ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን በጸሀፊነት ይሰራል ተብሎ መነገሩ ይታወቃል።

በዚህ መሠረትም 1000224609853 Swift code… cbetetaa በሚለው የባንክ ሂሳብ ቁጥር ሁሉም ሰው የድርሻውን መወጣት እንደሚችል ተነግሯል።

የአማራ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት በተሻሻለው የክልሉ ሕገ-መንግሥት አንቀፅ 58 ንዑስ አንቀጽ 7 እና የክልሉን አስፈጻሚ አካላት እንደገና ለማቋቋም፣ ለማደራጀት ብሎም ሥል ጣንና ተግባራቸውን ለመወሰን ተሻሽሎ በወጣው አዋጅ ቁጥር 230/2008 ዓ/ም በአንቀጽ 37 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህንን ደንብ አውጥቷል።

ዶክተር ሰለሞን ክብረት በዋሽንግተን ዲሲ የጣና ደህንነትን ለመጠበቅ የሚያስችል ግብረ ሰናይ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ሲሆኑ ከሰሞኑ በአማራ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት ከተቋቋመው የጣና ሀይቅ እና አካባቢው ደህንነት ፈንድ ጋር በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል።

በአሜሪካ የስነ-ህይወት ተመራማሪው ዶክተር ሰለሞን ክብረት የእንቦጭ አረም ነቀላ ወጀብ በሌለበት በጠዋት መሆን እንዳለበት አስገንዝበዋል።

የአማራ ክልል አካባቢ ፣ደን እና ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶክተር በላይነህ አየለም ጣና በስነህይወታዊ እና በማሽን ለመጠበቅ በተያዘው ወር ወደ ስራ ይገባል ብለዋል።

እስካሁን 1400 ሄክታር ከእንቦጭ ነፃ ማድረግ እንደተቻለም ገልፀዋል።