የአማራ ህዝብ የህወሃት የውስጥ ፖለቲካ ሚዛን ማስጠብቂያ እየሆነ ነው

Print Friendly, PDF & Email

(አያሌው መንበር)

ህወሃት የውስጥ ፖለቲካ ቀውስ ሲገጥማት ያንን ጉዳይ ከውጭ እንዳይሰማባት በማደረግ፣ የግጭቱ አካላት በሌላ ተግባር እንዲጠመዱ በማደረግ፣ አቅጣጫ በማሰቀየር፣ ወዘተ የክህሎት ልምዷ በአለም ላይ የሚያክላት የሌለ የሴረኝነት እና የተንኮል መሀንዲስ ነች። መለስ እድሜውን ሙሉ ሲሰራው ከኖረው ውስጥ እነዚህ ነገሮች ሰፊ ቦታ አላቸው። የመለስ የሴራ ራዕይ ደግሞ ግብአተ መሬቱም ተፈፅሞ አልቆመም።

የህወሃት ሴራ ፖለቲካ ማጠንጠኛው ከኤርትራ ቀጥሎ የአማራ ህዝብ መሆኑ መቸም የሚያወዛግብ አይደለም።ሁልጊዜ ትናንትሽ ቡድኖች ብዙሃኑን የሚገዙት ለብዙሃኑ ብዙ ጠላት በማፈራት አልያም ብዙሃኑ እንዳይንቀሳቀስ ዙሪያ ጥምጥም ወጥመድ በማጥመድ ተሸማቆ እንዲኖር በማደረግ ነው። የአማራን ህዝብ ወዳጅ አልባ ማድረጓ ሳያንስ አማራ ውስጣዊ ሰላም እንዳይኖረውም ሌት ተቀን ትደክማለች። ለህወሃት ሀገሪቱን እንዴት እናሳድጋት ከሚለው በላይ የአማራን ህዝብ እንዴት እናዳክመው? የሚለው ያሳስባታል።

ይህ የህወሃት ዘመን ቤተ ሙከራ የሆነ ህዝብ የፖለቲካ ትኩሳትም ማብረጃ ነው። አማራው በራሱ ተፈጥሯዊ እና ታሪካዊ ችግርን የመፍታት ልምድ ታግዞ እና ታግሶ ብዙ ችግሮችን ባያልፋቸው ኖሮ እስካሁን እልቂቱ ከዚህም በከፋ ነበር።በአፋር በኩል በሀብሩ ወረዳ፣ በኦሮሚያ በኩል በሰላሌ፣በቤኒሻንጉል በኩል በመተከል፣ በትግራይ በኩል በወልቃይትና ራያ፣ ከክልሉ ውጭ በረሀር፣ ኦሮሚያ፣ ሶማሌ ወዘተ ሁሉ የውስጥ ፖለቲካ ውዝግብ ሲነሳ የሚለኮሱ የክብሪት እንጨቶች አሉ። እነዚህ ሁሉ በቀላሉ መፈታት የሚችሉ የግጭት መንስኤዎች ህወሃት እንዲፈቱ አይፈልግም። የድንበርና ማንነት ጥያቄዎች ረገብ ሲሉ ደግሞ የኢኮኖሞ ጥያቄዎች የግጭት መንስኤ እንዲሆን ስትራቴጅ ይነድፋል። በዚህ ሁሉ ሂደት ግን ትግራይ ያለኮሽታ በግንባታ ላይ ናት።

እናም ህወሃት ሲሻው በአፍዴፓ ሲፈልግ በኦህዴድ አልያም በሶዴፓ እና በቤኒሻንጉሉ ፓርቲው የሚለኩሳቸው እንደየሁኔታው ሊጠፉ የሚችሉ እሳቶች ህወሃት የውስጥ ፖለቲካውን ሚዛን ይጠብቁለት ዘንድ የሚያቀጣጥላቸው ናቸው።

ህወሃት ባለፈው ወቅት በገጠማት የውስጥ ቀውስ ሶማሌና ኦሮሞን በማጋጨት እፎይታ ስታገኝ ኦህዴድን የቤትስራ በመስጠት በአንድ በኩል በውስጥ ጉዳዩ ላይ ብቻ እንዲያተኩር ለምዳረግ ሞክራለች። በሌላ በኩል ደግሞ “የክልሉን ህዝብ ሰላምና ፀጥታ ማስከበር ያልቻለ” ብላ ኦህዴድን ለመኮርኮም ትጠቀምበታለች። እዚህ ላይ ብአዴንና ደኢህዴን ምናልባት ወደ ኦህዴድ ቢወግኑ እንኳ “እናንተ ለህግና ስርዓት ተገዥ ያለሆነ፣ ለስርዓቱ ታማኝ ያልሆነ ሀይል ጋር እንዴት ትሰለፋላችሁ? በማለት ለማሸማቀቅና የኦህዴድን ጉልበት ለማዳከም አድርገዋለች። ይህ ለህወሃት ትልቅ ስኬቷ ነው። በዚህ ወቅት የኦሮሞና ሶማሌ ንፁሃን ዜጎች የህወሃት ፖለቲካ ሚዛን ማስጠበቂያ ሆኑ ማለት ነው። ምናልባት ብአዴን እዛ ላይጠንከር ብሎ ወደ ኦህዴድ ቢወግን ኑሮ ብአዴን ባይጎዳም አብዲ ኢሌን አማራዎችን ጨፍጭፍና ብአዴንን ትንሽ የቤት ስራ ልስጠው ማለቷ አይቀርም ነበር።ለነገሩ ባለመፈፀሙ አሁንም እርግጠኛ አይደለውም።ይህ ነገር የቀጣይ የቤት ስራዋም ነው።

ከዚህ ማግስት የተሻገረችው በኦሮሚያ እና አማራ ክልል #የድንበር ጥያቄ አለባቸው የተባሉና ብዙም ገፍተው ያልሄዱት የሰላሌ አካባቢ ላይ ግጭት በመፍጠር በአንድ በኩል ሁለቱን ድርጅቶች ማቃቃር በሌላ በኩል ደግሞ የአማራና ኦሮሞ ህዝብ ግንኙነት እንዲሻክር ነበር። ይህ ወቅትም ጉዳት ቢያደርም እንዳሰበችው አልሄደም። ልብ ሊባል የሚገባ ጉዳይ ህወሃት የተንኮል አራት አይና መሆኗ ነው። እዚህ አካባቢ ጥንቃቄ የተሞላበት ሴራን ከኦነግ/ከፊል ኦህዴድ ጋር ሁና ነበር የተወነችው።

#ሰላሌና ደራ ላይ ሲከሽፍ በተለይ ( ደራ ላይ የሰው ህይወትም ጠፍቶብናል) የዚሁ ክፍል ወደ ኢሊባቡር ተሸጋገረ።እዚህ ጋር ጠንከር ያለ የአማራ ጥላቻ ያለበት ከኦሮሞ ወገንም ተደራጀ። ከዚያም ወደ ጭፍጨፋ ተገባ።

#ኤሊባቡርና መቱ ላይ አሁንም ቀላል የማይባል ወገናችን ገብረናል። የተንኮል እናቷ ህወሃት ግን ንፁሃንን ገዳዮች ደህንነቶቸ ለምን ተያዙብኝ? በሚል አሁንም ሌላ ነገር ፈለገች። ምናልባትም የአማራ ክልል መንግስት በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ከክልሉ ውጭ ላሉ አማራዎች ያገባኛል በሚል (በኦህዴድ ግብዣ ነው ይባላል) ወደ ቦታው መጓዙ አልተዋጠላት ይሆናል።

በሌላ በኩልም ሚዛን ማስጠበቂያው ጆከሩ ብአዴን ገና ያለየለት መሆኑ ይሁን ሌላ ባላታወቀ ምክንያት ሳይውል ሳያድር የዛሬ ሁለት ኣመት አለምን ጉድ ያስባለ አማራዎች ላይ ወንጀል የተፈፀመበት ቤኒሻንጉልን ድጋሚ አማተረችው። ወረዳውን ባላስታውሰውም የሶማሌው ግጭት ሰሞን እዚሁ #ቤኒሻንጉል ክልል የትግራይ ባለሀብቶች የሚኖሩበት አካባቢ ያሉ ደህንነቶች አማራዎች ላይ ትንኮሳ ጀምረው በቶሎ እንደተቀጨ የተረጋገጠ መረጃ ነበር። እንግዲህ የዚህ ክፍል ይመስላል ከሶስት ቀናት ማስፈራሪያ በኋላ #በካማሽ ዞን አንድ ወረዳ ውስጥ በአማራዎች ላይ እጅግ ለመግለፅ የሚዘገንን ወንጀል ተፈፀመ። ወገኖቻችን በገጀራ፣ በቀስት፣ በጩቤ ተገደሉ። ገደል ውስጥም ተጨመሩ። ቤት ውስጥም እሳት የነደደባቸው እንዳሉ እየተነገረ ነው። ይህ ድርጊት ሲፈፀም የክልሉ ልዩ ሀይል፣የወረዳው አመራሮችና የፀጥታ ሀላፊ ከቦታው ነበሩ። የወረዳው ፀጥታ ሀላፊ 2000ዓ.ም አማራዎች እዛው ቦታ ሲፈናቀሉ መሪ ተዋናይ የነበረ መሆኑ ተረጋግጧል።

በዚህ ሁሉ ድርጊት አማራው በክልሉ ውስጥም ከክልሉ ውጭም በሰላም እንዳይኖር ሌት ተቀን የምትሰራው ህወሃት የለችም ማለት የዋህነት ነው። ህወሃት ትልቁ ስራዋ አማራውን በኢኮኖሚ ማድቀቅ፣ ጠላት ማብዛትና የውስጥ ሰላም እዳይኖረው ማደረግ ነው።

ህወሃት አማራ ላይ በኦሮሚያ እና ቤኒሻንጉል ከሞከረችው በተጨማሪ #አፋር ላይም ይህንኑ ለመድገም እየተንቀሳቀሰችያ መሆኑ መረዝጃዎች እየወጡ ነው።በሀብሩ ወረዳ በኩል ውጥረት መንገሱ እየተነገረ ነው።
ይህ ጉዳይ ቀጣይና የአማራ እጣ ፈንታ ከሆነ ሰነባብቷል።

ብዙዎቻችን በደንብ ባንገነዘበውም የአማራ ህዝብ የህወሃት የፖለቲካ ሚዛን ማስጠበቂያ እየተደረገ ለብዙ አመታት ዘልቋል። አሁንም በተጨባጭ እየሆነ ያለው ይህ ነው። ህወሃት እና ኦህዴድ ለጎሪጥ መተያየት መጀመራቸው ብአዴንን በጆከርነት ለማጫወት አልያም ለራሱ የማይወጣው የቤት ስራ ለመስጠት ሲባል ህወሃት የአማራን ህዝብ ቁማር ረክዛ እየተጫወተች ትገኛለች። ህወሃት ስልጣኗን እስካራዘመላት ጊዜ መላ የኢትዮጵያን ህዝብ መረከዟ አይቀርም። እየሆነ ያለውም ይህ ነው።

እናም አሁን በተለያዩ አካባቢዎች የተከሰተው አማራ ላይ ያነጣጠረ ግጭት የህወሃት የፖለቲካ ልብ ትርታ መለኪያና ትኩሳት ማብረጃ ነው። ይህ እንደየ ሁኔታው በሌላ ቦታም መከሰቱ አይቀርም። ይህንን ለማደረግ እየተዘጋጀችም ነው።
እመኑኝ የቤኒሸንጉሉ ጭፍጨፋ አሁንም ወደ አፈር ድንበር በፍጥነት እየተጓዘ እየገሰገሰ ነው።

የአማራ ህዝብን እየጨፈጨፉ የፖለቲካ ቁማር ይበቃ ዘንድ መፍትሄው የህወሃትን የሴራ ፖለቲካል በደንብ መገዘንብና በአማራነት መቆም ነው።

 

በኢልባቡር ከግድያ የተረፍና የተፈናቀሉ አማሮች

በኢልባቡር ከግድያ የተረፍና የተፈናቀሉ አማሮች

በኢልባቡር ከግድያ የተረፍና የተፈናቀሉ አማሮች