በሕዝባችን ላይ እየደረሰ ያለውን ግድያ ለመታደግ በጋራ እንቁም!! – የኢሕአግ መግለጫ

Print Friendly, PDF & Email

ከኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኛ ግንባር የተሰጠ መግለጫ (pdf)
ቀን፦ ጥቅምት 17/2010

በሕዝባችን ላይ እየደረሰ ያለውን ግድያ ለመታደግ በጋራ እንቁም!!

መራሹ የወያኔ ኢሃዴግ አገዛዝ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እያደረሰ ያለውን ግድያ ለማስቆም ሁሉም በጋራ ሊንቆም ይገባል።

ሕዝባችንን ፈጥነን ከወደቀበት አደጋ ልናስጥለው የሁላችንንም ርብርብ ያስፈልጋል!

የሃገራችን ኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ እጅግ በጣም አሳሳቢ ደረጃ ላይ በደረሰበት በዚህ ሰዓት ሕዝባችን ከወደቀበት አደጋ ልንታደገው የሁላችንም ተሳትፎ ወሳኝ ነው።

የሕዝብ ጥያቄን በአግባቡ ማስተናገድ ያልቻለው መራሹ የወያኔ ኢሃዴግ አስተዳደር አሁንም ትንሽ ትልቅ ሳይል ከልጅ እስከ አዋቂ ፣ወንድ ሴት ሳይመርጥ በርካቶችን ገድሎአል ፣አቁስሏል ብዙዎችን አስሯል።

በመሆኑም ይህን እኩይ ተግባሩን ሳይፈራና ሳይሸሽ በመጋፈጥ ግንባሩን እየሰጠ ላለው ለአምቦ ጀግና ሕዝብ ለጎንደርና ባህርዳር ወጣት ልንደርስለት ይገባል።

ሰረዓቱን ለማስወገድ ከሕዝብ ጋር ተቀላቅለን ፣ቆርጠን በመነሳት የምንረባረብበት ጊዜ አሁን ነው ።

የወያኔ ስረዓት ሃገርን በትኖ ለመሄድ በመንገድ ላይ ይገኛል። ለዚህም ምልክቱ ቱባ ቱባ ስልጣን የተሸከሙት ቀንድ ባለስልጣኖች ስልጣን በመልቀቅና በመፈርጠጥ ላይ ይገኛሉ።

ከዚህም በላይ የኢሃዴግ ስረዓት ፈርሷል ! የህውሃት ፓርቲም በመፈራረስ የመጨረሻውን የሃይል ሩጫ ሃገርን በመበታተንና ህዝብን በማጋጨት ተራ ስራ ላይ ይገኛል።

በመሆኑም ይህንን ሰው በላ የወያኔ ኢሃዴግ ስረዓት መወገጃው ጊዜ በጣም ጥቂት ጊዚያት በሆነበት በዚህ ወቅት ሃገሪቱንና ሕዝቧን ለመበታተንና ከማንወጣበት የሕዝብ ዕልቂት ውስጥ ለመክተት እየተፈራገጠ ይገኛል።

በመሆኑም በሃገር ወስጥና በውጪ ሃገር የምትገኙ ውድ ኢትዮጵያዊያንና የኢትዮጵያዊያን ቤተሰቦች ጥሪያችንን የጋራ በማድረግ ህብረተሰባችንን ከተጫነው አደጋ ልንታደገውና ትግላችንን ታሪካዊ ማድረግ ይጠበቅብናል።

ይዋል ይደር እንጂ ዛሬ በዜጎቻችን ላይ እጃቸውን የሰነዘሩና ያስነዘሩ ለፍርድ የሚቀርቡበት ወቅት በመቅረቡ ሁላችንም የድርጊቱን ባለሟሎች ከህግ ፊት ለማቅረብ በየ ቦታው ያላችሁ አርበኞች ዝግጅት እንድታደርጉ እናስገነዝባለን።

አንድነት ሀይል ነው!
የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር