የሐዘን መግለጫ! – የአማራ ማህበረሰብ በዲሲ፣ ቨርጂኒያ እና ሜሪላንድ

Print Friendly, PDF & Email

የሐዘን መግለጫ! – የአማራ ማህበረሰብ በዲሲ፣ ቨርጂኒያ እና ሜሪላንድ

በኢሊባቡር በአማራ ህዝብ ተወላጆች ላይ እየደረሰ ባለው ጭፍጨፋ በአሰቃቂ ሁኔታ በተገደሉት ወገኖቻችን የተሰማንን ከፍተኛ ሐዘን እንገልጻለን።

የቅድመ ትግል መስመሩንና አሁንም የአስተዳደር መርሁን የአማራን ሕዝብ በማዳከምና በማጥፋት እንዲሁም የሃገሪቱን አንጡረሃብት በመዝረፍ ላይ ያተኮረው የወያኔ ቡድን ዛሬም እንደትላንቱ መልኩን በመቀያየር የአማራን ሕዝብ በግፍ በመግደልና በማስገደል ተግባር ላይ ይገኛል። ትላንት በበደኖ፣ በአርባጉጉ ፣ በቤንች ማጅ፣ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ፣ በጅጅጋ፣ በምስራቅ ሃረርጌ የተለያዩ ቦታዎች ፣ በወለጋ ፣ በጅማ ፣ በወልቃይትና በጠገዴ ብሎም በተለያዩ የሃገሪቱ አካባቢዎች በህውሃት መሪነትና በጀሌዎቹ አጋፋሪነት የፈሰሰው የወገኖቻችን ደም እንደ እግር እሳት አያቃጠለን ባለበት በዚህ ሰዓት የአማራን ደም ጠጥቶ ያልጠገበው የወያኔ ቡድን በኢሊባቡር በተቀናበረ መንገድ አማሮችን በግፍ በማስገደልና በማሳደድ ላይ ይገኛል።

ወያኔ የአማራ ሕዝብ አንደትላንቱ በደሉን በዝምታ ውጦ የሚቀመጥ ሳይሆን መስዋትነትን ከፍሎ ነጻ የሚጣበት መስመር ላይ መሆኑን በመገንዘብ የወገኖቻችን ደም ከማፍሰስና ይህንን ወንጀል ከማቀናበር እኩይ ተግባሩ እንዲታቀብ እናሳስባለን። ማንኛውም በተለያየ ደረጃ ከዚህ መንግስት ጋር የሚተባበርና በወገኖቻችን ላይ እጁን የሚያነሳ ግለሰብና ቡድን እስከ ዘመኑ ፍጻሜ ድረስ ከጸሃይ በታች የምንፋረደው መሆኑን በመገንዘብ እራሱን ከዚህ አኩይ ተግባር እንዲያገልና ከንጹሃን ዜጎች ጎን እንዲቆም በአንክሮ እናሳስባለን።

በየትኛውም ቦታ በግፍ የሚፈሰው የአማራ ደም ከፍተኛ ዋጋ የሚያስከፍል መሆኑን ለነገ የእውነት ምስክር የሚሆን የታሪክ መዝገብ በዚህ የሃዘን መግለጫ ታትሞ አንዲቀመጥ አድርገናል።

እግዚሃብሄር የንጹሃኑን ንብስ በአጸደ ገነት ያኑር !
የአማራ ሕዝብ በትግሉ ነጻነቱን ያገኛል !