አስቸኳይ መልዕክት ከጎንደር ቤተ ክህነት

Print Friendly, PDF & Email

አስቸኳይ መልዕክት ከጎንደር ቤተ ክህነት በጎንደር አቡን ቤት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም በይሰሞን በተፈጠረው የደብሩ አስተዳዳሪን የማውረድ እንቅስቃሴ ጀርባ ያሉ ድብቅ የአማራን ተጋድሎ ለመጎተት የተዘጋጀ ሰይጣን የህወሃት ሴራ።

በጎንደር አቡን ቤት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም በይሰሞን በተፈጠረው የደብሩ አስተዳዳሪን የማውረድ እንቅስቃሴ ጀርባ ያሉ ድብቅ የአማራን ተጋድሎ ለመጎተት የተዘጋጀ የህወሃት ሴራ።

በቅርቡ ከሦስት ሳምንታት በፊት በጎንደር አቡን ቤት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ውስጥ የሚገኙ ሁለት አጥማቂዎች በደብሩ አስተዳዳሪ መላከ ኃይል ቆሞስ አባ ገብረ እግዚአብሔር አስተዳዳር በመማረራቸው የፀበሉን አገልግሎት ትተው ሂደዋል።

ይህንንም ተከትሎ በአጥቢያው የሚገኘው ህዝብ አለቃውን በመቃወም ከፍተኛ እንቅስቃሴ በማድረጉ ነገሮች እስከሚጣሩ በሚል አለቃው በብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ እንዲታገድ ተደርጓል። በዚህ የህዝቡ እንቅስቃሴ የመንግሥት የጸጥታ መዋቅሮች ትልቅ ራስ ምታት ሁኗቸው ጉዳዩን ከከተማ እስከ ክልል ድረስ አሁንም ድረስ ጉዳዩ በከፍተኛ ምስጢርና በጥንቃቄ መያዙን ከመንግስት አካላት የሚደርሱ መንጮች ይገልጻሉ። በተለይም ከጉዳዩ ጋር ፖሊቲካዊ ተልዕኮ ይኖራቸዋል የተባሉ 16 የኮሚቴ አባላት ክትትል እየተረገባቸው ነው። ለህዝቡም ሆነ ለ16 የህዝብ ተወካይ ለተባሉ ኮሚቴዎች ከጀርባ ያለውን የህወሃት ሴራ እንዲህ ነው።

ነገሩ እንዲህ ነው፤ በሰሜን ጎንደር ዞን ሀገረ ስብከት ዋና ፀሐፊ የነበሩት መላከ ህይወት ቀለመ ወርቅ ዓለሙ በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ አማካኝነት ከሥራ መነሳታቸውን ተከትሎ ግለሰቡ በጎጠኝነት መንፈስ በመነሳት ‹‹ ወገራ በደብረ ታቦር ተንቋል፤ እንግዲህ ወገራ የሆንክ ሁሉ ና!! ሀገረ ስብከቱ ደብረ ታቦር ጨፈረበት በማለት›› በየአብያተ ክርስቲያናቱ የሚገኙ የወገራ ተወላጆችን በመቀስቀስ ከፍተኛ እንቅስቃሴ አደረጉ።

አብዛኛውን የግለሰቡን ችግር ስለሚያውቁ የዓላማው ተባባሪ ባይሆኑም የተወሰኑት ግን በሰልፍ ወደ ሀገረ ስብከት በመሄድ ጎንደርን ባጠበበ መንፈስ ‹‹ ወገራ ›› በሚል መንፈስ ሊቀ ጳጳሱን በመቃወም ለማንሳት ከፍተኛ እንቅስቃሴ አደረጉ። በዚህ እንቅስቃሴ ግንባር ቀደም ሚና የነበራቸው ከሁለቱ አጥማቂዎች መካከል አባ ወልደ ሰንበት የሚባሉት ናቸው። በዚሁ ሀገረ ስብከት ደብረ ታቦር ብቻ የሚል መንፈስ ያላቸው ግለሰቦች እንዳሉ የሚታመን ሲሆን ዓላማቸውንና እነማን እንደሆኑ በኋላ እንመለስበታለን።

ወደ ቀደመ ነገራችን ስንመለስ ቀለመ ወርቅ የታበለው ግለሰብ ከሀገረ ስብከት ፀሐፊነት ከተነሳ በኋላ ጠባባብ የሆኑ ግለሰቦችን በመያዝ ውስጥ ለውስጥ የወገራ ቡድን ማደራጀት ጀመረ። ይህን ሥራ ከሀገረ ስብከቱ ሰንበት ት/ቤት ክፍል ኃላፊ መጋቤ ላዕካን ዘካርያስ ያዕቆብ ጋር በመሆን ማስተባባር ቀጠለ። ይህንንም የአቡነ ኤልሳዕን የማስነሳትና ተራ ጎንደርን ወደ ጎጥ የመከፋፈል እንቅስቃሴ ሊያግዝ የሚችል መንገድ ሲፈልጉ ቆዩ።

በኋላም ጎንደር ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ህዝበ ክርስቲያኑ በአለቃው መማረራቸውን እንደትለቅ አጋጣሚ በመጠቀም በአባ ወልደ ሰንበት ጠንሳሽነት/ ቀለመ ወርቅ ወገራ ስለሆነ ለምን ከፀሐፊነቱ ይነሳል በማለት ሲታገል የቆየው/ ‹ ፀበሉ ላይ ተጠማቂዎች ታፈኑ፤ አስተዳዳሪው ባለቸው ፖለቲካዊ አቋም ሊያሰሩን አልቻሉም›› የሚሉ ምክንያቶችን በመጥቀስ ምንም የማያውቁትን ባህታዊ አባ ኃ/ማርያም ቀስቀስሰው ከጎንደር ወደ አዲስ አበባ ጸበሉን ለቀው ሂደዋል።

ይህንንም ተከትሎ የጸበሉ ወዳጆች፣ የአባ ወልደ ሰንበት የንስሐ ልጆች ሌሎች በአማራነት ሳይሆን በጎጥ የሚያምኑ የወገራ ተወላጅ ካህናት አስተዳዳሪው ከፍተኛ የደብሩ ሥጋት መሆኑን በማንሳት ህዝቡ እንዲነሳ ከፍተኛ ቅስቀሳ አደረጉ። ህዝቡም በየአካባቢው ተሰበሰበ አስተዳዳሪውን በከፍተኛ ሁኔታ ተቃውሞ ደብሩ ላይ በተደረጉ ተከታታይ ስብሰባዎች 16 የኮሚቴ አባላት ተመረጡ።

ይህንን እንቅስቃሴ የሚመራቀው ቀለመ ወርቅ ዓለሙ የተባለው የቀድሞ ፀሐፊ ነው። ህዘቡ አስተዳዳሪው ይነሳ የሚል ጥያቄ ያለው ሲሆን ቀለመ ወርቅ ዓላማው ግን ህዝቡን ተጠቅሞ በአቡነ ኤልሳዕ ላይ ተቃውሞ እንደተነሳ በማስመሰል ‹‹ ሰሜን፤ ደቡብ›› በማለት የራሱን ጥቅም ለማስጠበቅ ነበር። ይህንን ጉዳይ በከፍተኛ ሁኔታ ተቃውማ በህዝቡ ላይ ይቀሰቅሳል በማለት የመንግስት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጉዳዩን መከታታል ጀመሩ።

ለአለቃው እንዲነሳ የተሰበሰበውን ፊርማ ለአቡነ ኤልሳዕ የቀረበ ተቃውሞ በማስመሰል ወደ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ልከውታል። ይህም ደቡብና ሰሜን እንዲከፋፋል የተዘጋጀ ሴራ ነው።

የህወሃት ሴራ፦

ህወሃት የከተማውንና የዞንኑን ሆድ አደር የፀጥታ አካላትን በመጠቀም ቅዱስ ገብርኤል ገዳም የሚታየውን ችግር እንደትልቅ አጋጣሚ በመውሰድ ሰሜን ደቡብ ብሎ ካህናቱን ብሎም ህዝቡን በመከፋፋል የአማራን ተጋድሎ ለመቀለበስ ከፍተኛ ሥራ እየሰራ ይገኛል። የመንግስት ባለሥልጣናትንም ሰሜን ደቡብ በማለት እርስ በእርስ እንዲከፋፈሉ በማድረግ ላይ ይገኛል። ለዚህም ጎንደር ላይ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ላይ የተፈጠረውን ችግር እንዲበርድ አለመፈለጉ ማሳያ ነው። ትኩረት ሊደረግባቸው የሚገባቸው ግለሰቦችመላከ ህይወት ቀለመ ወርቅ ዓለሙ፤- ይህ ግለሰብ ጎንደር ላይ በነበረው ትግል የሀገረ ስብከቱን ሥራ አስኪያጅ‹‹ ኮከብ ያለበት ባንዴራ በጽ/ቤቱ ላይ ሰቅሏል›› በማለት ሊቀ አእላፍ ቀለመ ወርቅ አሻግሬን ለህወሃት አሳልፎ በመስጠት ከስድስት ወር በላይ እንዲታሰር ያደረገ። ሀገረ ስብከቱን ከህወሃት በሚሰጠው መመሪያ መሰረት ሰሜን እና ደበቡ በማለት ክፍፍል እየፈጠረ የፈጠረ።በወልቃይት ጉዳይ ህዝቡን መሳሪያ አታንሱ ብሎ በህወሃት እንዲወረሩ ያደረገ።

መጋቤ ላዕካን ዘካሪያስ ያዕቆብ፤- በቤተ ክህነቱ ውስጥ ‹‹ ይሁዳ ›› የሚል ቅጥል ስም የተሰጠው ሲሆን የቅማንት ተወላጅ ነው። አማራን ከቅማንት ጋር ለማጣላት ከፍተኛ ሥራ ሲሰራ የቆየ። አሁን እየተፈጠረ ባለው ችግር ከቀለመ ወርቅ ጋር በመሆን ጎንደር ላይ የአማራ ትግል እንዲቀዘቅዝ ከፍተኛ ሥራ በቤተ ክህነቱ እየሰራ የሚገኝ አባ ወልደ ሰንበት /አጥማቂው/፤- የነ ቀለመ ወርቅ ዓለሙን ሴራ ተግባራዊ በማድረግ ህዝቡ በጎጠንነት መንፈስ እንዲነሳሳ ቅስቀሳ የሚያደረግ። ሊቀ ጉባዔ አስካል፤- ሰሜን ደቡብ በማለት ክፍፍሉ እንዲስፋፋ ከፍተኛ ሥራ የሚሰራ። ‹‹ በአንድ ኮነሬል ምክንያት ጎንደር ተበጥብጣለች፤ ከዚህ በኋላ ሁሉም ጸጥ ቦሎ ለመንግስት መገዛት አለበት›› በማለት አማራ ተጋድሎ ፤የፈሰሰው ደም ምንም ትርጉም እንደሌለው እየገለጸ የሚገኘ

ማጠቃለያ ለጎንደር ህዝብ፦

ጎንደር ላይ ከላይ የተጠቀሱት እና ሌሎች በውስጥ ሆነው የህወሃትን ሴራ ተቀብለው ሰሜንና ደቡብ በማለት ካህናቱንና ህዝቡን በጎጠንነት መንፈስ ለማነከስ ሌት ተቀን የሚሰሩ ግለሰቦችን በዓይነ ቁራኛ በመከታተል አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወስድ ጎንደር አቡን ቤት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ውስጥ የህወሃት ደህንነት ሆነው ደብሩን ሲያስተዳዳሩ ነበሩት መላከ ኃይል ቆሞስ አባ ገብር እግዚአብሔር ደምሌ የተባሉት ግለሰብ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እርምጃ እንዲወሰድባቸው።

አሁን ተጀመሩው አማራ ትግል ከጫፍ ሊደረስ የሚችለው ሰሜንና ከደቡብ በአብሮነት መንፈስ ሲቀጥል መሆኑ ግልጽ ነው። በመሆኑም ይህንን አንድነታችንን በጎጠኝነት መንፈስ ተይዘው በህወሃት ተደልለው፤ ከሚመጡ ካህናት ሁላችንም ራሳችንን ልንጠበቅ ይገባናል።

አማራ!! ጎንደር፣ ጎጃም፤ ወሎ፤ ሽዋ በጋራ ወደ ፊት
ድል ለአማራ ሕዝብ!!