ግራዝማች ናደው ወረታ የስሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ መስራች ይታወሳሉ

Print Friendly, PDF & Email

የስሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ በፓርክነት የተመዘገበበትን 50ኛ ዓመት የአማራው ፕሬዘዳንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በተገኙበት በደባርቅ ከተማ በደማቅ መከበሩን በተለያዩ መንግስታዊ ሚዲያዎች በ”ደማቅ” እየተዘገበ ነው።

ግራዝማች ናደው ወረታ የስሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ መስራች

ይህን የሰሜን ተራሮች ድንቅየ የኢትዮጵያ የተፈጥሮ ሀብት ገና በቀዳማዊ ሀ/ስላሴ ግዜ አርቀው በማሰብ ሰሜኗ ኢትዮጵያ የቱሪዝም መናሃሪያ ትሆናለች ብለው የመሰረቷት ድንቅየ ኢትዮጵያዊ ግራዝማች ናደው ወረታ አንድም ግዜ ስማቸው አለመነሳቱ ያሳዝናል!!! “እምየ ኢትዮጵያ ሞኝነሽ ተላላ የሞተልሽ ሳለ የገደለሽ በላ!” የሚለው አባባላችን ሁኔታውን ይገልፀዋል።እስኪ ስለግራዝማች ናደው ወረታ የስሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ በፓርክነት የተመዘገበበትን 50ኛ ዓመት በማስመልከት እችን እውነታ አንብቡ ። (የቀኛአዝማች እያዩ ወረታ የልጅ ልጅ ነኝ) ።

ኢትዮጵያ የብዙ ጀግኖች ማፍሪያ የታሪክ ማህደሯ በጀግኖች ታሪክ የሞላ አሁንም በጀግኖች የታጠረች አገር ናት::ዛሬ ከጀግኖቻችን አንዱ ስለሆኑት ግራዝማች ናደው ወረታ የጀግንነት ታሪክበአጭሩ ለመዘከር እንሞክራለን:: ግራዝማች ናደው ወረታ ቢትዮጵያ የሰሜን ተራሮች በጎንደር ክፍለሃገር በልዩ ስፍራ አምባራስ በሚባል አከባቢ ተወለዱ::ለአቅመ አዳም እስኪደርሱ ድረስ በአከባቢያቸው ጠንካራ ስራዎችን woreta ሲሰሩ የነበሩት ግራዝማች ታላላቅ ስራዎችን ሰርተው አልፈዋል:: የአከባቢው አስተዳዳሪ ሆነው የተሾሙት ግራዝማች ናደው በአጼ ሃይልስላሴ ዘመን የፓርላማ አባል በመሆን ያገለገሉ ሲሆን ታላቅ ፖለቲከኛ ሕግ አውጪ እና አማካሪ ጠበቃ በመሆን ታላቅ ስራዎችን ለሕዝባቸው አበርክተዋል::

ከዚህ ጋር በተያያዘ የሰሜን ተራሮችን ፓርክ በመመስረት ረገድ ከፍተኛውን እና ግንባር ቀደም ሚና ተጫውተዋል::የአከባቢውን ነዋሪዎች በማስተማር በማስተባበር በማቀናጀት ከመጀመሪያ ጀምሮ የደን ጭፍጨፋን ስለመከላከል የደን ጥበቃን ወዘተረፈ በማስተማር የፓርኩ ዋና ተንከባካቢ በመሆን ድርሻቸውን አበርክተዋል:: በተፈጥሮ መልካምነትን ያደላቸው ግራዝማች ናደው እጅግ ሩህሩህ ያላቸውን የሚያካፍሉ ለሰው አዛኝ ረዳት እና ታታሪ ነበሩ:: በሃገራችን አንድ የተለመደ ነገር አለ ለህዝብ እና ለሃገር አስታውጾ ያበረከቱ እና የጥሩ ጀግኖች አስታዋሽ ማጣታቸውን እና መልካም ዋጋቸውን አለማግኘታቸው የሚያሳዝን ጉዳይ ነው::ግራዝማች ቢያልፉም ስራቸው ህያው ሆኖ ይታወሳል በተግባርም እየታይ ሌላዉንም እያበረታታ ነው::

የሰሜን ተራሮች ፓርክን ለቱሪዝም መስሕብነት በማብቃት በዛሬው ጊዜ ላይ በሺዎች የሚቆተሩ ቱሪስቶች ፓርኩን በመጎብኘት ለሃገሪቱ የውጪ ምንዛሬ ግኝት የግራዝማች ፈር ቀዳጅነት የማይረሳ ታላቅ ስራ ነው::እንዲሁም በፓርኩ ውስጥ በቱሪዝም መስክ በርካታ የስራ እድሎችን ለዜጎች በመክፈት ታላቅ ስራ ሰርተው አልፈዋል::ይህ ስራቸው ከተወሰኑ ሰዎች እና ከቤተሰባቸው ታሪኩ ሊነገር አለመቻሉ እስካሁን በሰፊው ሳይነሳ ቆይቷል:: ግራዝማች በሕይወት ባርኖሩም ለቤተሰባቸው ትተው ባለፉት ጥንካሬ እና በምክር የተገነባ የሞራል ታላቅነት እሳቸው ሌናት ሃገራቸው ያደረጉት አስታውጾ እና ለሕዝባቸው በሰሩት መልካም ስራ ሲያስታውሳቸው መጭው ትውልድ እንዲበረታታ እንዲንቀሳቀስ እና የተረሱ ጀግኖች እንዲታወሱ የጋራ የሆነ የዜግነት ሃላፊነት አለብን::

ስልዚህ እንደ EWCA እና እንደ ፓርክ ጽ/ቤቶች ያሉ ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት እና ሌሎች ለጉዳዩ አትኩሮት በመስጠት ለፓርኩ እድገት የሚደረጉ ስራዎችን በማስፋት እና በማዳበር ሰፊ ስራዎች እንዲሰሩ አገራዊ ግዴታችንን በአንድነት ልንወጣ ይገባል:: በመጨረሻ ለማለት የምፈልገው ለግራዝማች ናደው ወረታ እና ለቤተሰባቸው ያለኝን ጥልቅ አድናቆት እየገለጽኩ ለሰሜን ተራሮች ፓርክ መመስረት ላበረከቱት አስታውጾ እያደነኩ ግራዝማች ያልተነገሩ ብዙ ታሪኮች ያሏቸው ሲሆኑ ወደፊት በሰፊው የምመለስበት ሲሆን ለዛሬው በዚህ ይብቃን:: ፈጣሪ ውለታቸውን ይክፍላቸው ነብሳቸውን ይማር ::ከአክብሮት ጋር::

የሰሜንን ፓርክ ለቱሪዝም መናህሪያ ያደረጉት እና ሰሜን ፓርክን የመሰረቱት ድንቅየ ኢትዮጵያዊ ግራዝማች ናደው ወረታ እኒህ ናቸው ::

ክብር ለሚገባው ክብር እንስጥ!!!