የካሣ ተ/ብርሃን የወረደ ስብዕ እና አበርጌሌ

Print Friendly, PDF & Email

(ሙሉቀን ተስፋው)

የትግራይ ጠባብ ብሔርተኞች ክልሎችን ሲያካልሉ በጊዜው የሚያውቁትንና ዐይናቸው ያረፈበትን የዐማራ መሬት መውሰዳቸው የታወቀ ነገር ነው፤ በጊዜው ወደ ትግራይ ማዕከላዊ ዞን የተመደበው አንደኛው የዋግኽምራ አካል የሆነው አበርጌሌ ነው። አበርጌሌን ትግሬዎች ሲወስዱ ካሣ ተ/ብርሃን የተጫወተው ሚና ከፍተኛ ነበር።

በእነ ካሣና በሕወሓት ግብረ አበሮቹ አበርጌሌ ከሁለት ተከፈለ። እንደ እንደ ጎንደሩ ጠለምትና ጠገዴ አካባቢዎች አበርጌሌ ትግረውና አበርጌሌ ዐማራው ተብለው የወሎ አገዎች ከሁለት ተከፈሉ። አበርጌሌ ሁለቱም ወረዳዎች ሙሉ በሙሉ የዋግሹሞች አገር ቢሆን በግዴታ እንደወልቃይትና ጠገዴ ዐማሮች በግዴታ ትግሬዎች ናችሁ ተብለው ለዓመታት ታፍነው ቆዩ።

በ2001 ዓ.ም. የተከዜን ግድብ ለመገደብ ሲታቀድ የተጠናው ጥናት ግድቡ ከፍተኛ ኃይል ማመንጨት የሚችለው ዋግኽምራ ላይ እንደሆነ አመለከተ። በእነ ካሣና መለስ ከአበርጌሌ ርቆ ተገደበ። ሆኖም ተፈጥሮ አሁንም ለዋግሹሞች አደላና አብዛኛው የሐይቁ ክፍል ወደ ዋግ አበርጌሌ ተቋተ። ሐይቁ አበርጌሌን (የዐማራውን አበርጌሌ ጨምሮ) አዲስ የውኃ አካል ሲፈጠር ከቀረው የዋግ ክፍል ነጠለው።
አበርጌሌዎች ድልድይ እንዲሠራላቸው ብአዴኖችን ጠየቁ። መሠረት ድንጋይ ለማስቀመጥ የሚሆናቸው የለምና የመሠረት ድንጋይ ተቀምጦ ይሠራል ተብሎ 10 ዓመታት እንደዋዛ አለፉ።

ሕወሓቶች ደረቅ መሬት ነው ብለው ንቀው የተውት (የዐማራው) አበርጌሌ ከሰው ሠራሹ ሐይቅ በተጨማሪ ከፍተኛ መጠን ያለው የወርቅ፣ የብረትና የፖታሽ ማዕድን ተገኘ። ይኼኔ እንደገና የሕወሓቶች ምራቅ በጉምዣት ተዥረበረበ።

በእነ ካሣ ተ/ብርሃን አጋፋሪነት ሕወሓቶች መጀመሪያ ስብሰባችን ያካሔድንባት ቦታ አበርጌሌ ስለሆነ ወደ ትግራይ ትካለል ብለው ለፌደሬሽን ምክር ቤት አመለከቱ። አበርጌሌ ብአዴንም ባዕድ ሆኖ ድልድይ ሳይሠራ ወንዝ ወዲያ ማዶ ከባዕድ ጋር አዛምዷቸው ሕወሓቶችም ከነገ ዛሬ እንጠቀልላታለን ሲሉ እየተያዩባት አበርጌሌ አለች።

ካሣ ተ/ብርሃን የወረደ ስብእና፤

ካሣ ተ/ብርሃን እንኳን አገር የሞተ ሰው አስከሬን ይሸጣል፤ ከሆስፒታሎች አስከሬን እያወጣ ለቲችንግ ሆስፒታሎች እንደሚሸጥ ሁሉ በርካታ ማስረጃዎች አሉ። ሥልጣኑን ተጠቅሞ የብዙ ባለሀብቶችንና የብአዴን ባለሥልጣናትን ሚስት የቀማ ስብእናው የዘቀጠ ሰው እንደ ካሣ ተ/ብርሃን የለም። አቶ ያየህ አዲስ የተባለው የርዕሰ መስተዳደር ጸ/ቤት ኃላፊ የሆነው ወደ ሥልጣን ለመምጣት ባለቤቱን ለካሣ እጅ መንሻ አቅርቧል። ካሣ ከጋምቢ ሆስፒታል ባለቤቶች አንዱ የሆነውን የዶክተር ገበያውን ባለቤት በውሽማ ይዞ ከቆየ በኋላ ሀብቷን አካፍሎ ጠቅልሎ ነው የወሰዳት።

የካሣን ስብዕና ከዚህ በላይ በጣም የሚያሳዝኑና የዘቀጡ ባሕሪያት ከነሙሉ ማስረጃቸው ነበሩኝ። ግን የካሣን ስብእና ስንገልጥ ብዙ ሰዎች ሞራላዊና አእምሯዊ ጉዳት ሊያስከትል ስለሚችል ለጊዜው በዚህ ትተነዋል። ወደፊት እንደአስፈላጊነቱ እየተጠነቀቅን እንገልጸዋለን።