እግዚኦ! አልወለድም ! ለምን ልወለድ !? ጦቢያ !!!

Print Friendly, PDF & Email

በጎጠኛ አገዛዝ አልወለድም፤ ለሁሉ እኩል ተብሎ የተደነገገው ህግ እንኳ ባፈፃፀሙ እንደ ሰዎች ሁኔታ የሚሄድ፤ የአገሪቱ ተወላጆች ኢትዮጵያውያን በእኩልነትን በነፃ የሚያገኙት አየርንና የፀሀይ ብርሃንን ብቻ ነው፤ የህዝብና የአገር ሀብት በጥቂቶችዝርፊያ ቁጥጥር ስርይገኛል። ኢትዮጵያ በታሪኳ ታይቶ በማይታወቅ አረመኔ አውሬ የ‘ሰይጣን’ ጎጥ ፖለቲካ በአንድ ብሄረሰብፍፁም አምባገነናዊ አገዛዝ ከአራት ኪሎ ቤተመንግስት አዛዥ እስከወታደራዊ የበላይ መኮንኖች፤ ከመንግስት ተቋማት ባለስልጣናት እስከ ክፍለ ሀገር፤ ወረዳና ቀበሌ አስተዳዳሪዎች በህዝባዊ ወያኔ አባሎች ስር ወድቃ ትገኛለች።

ዴሞክራሲያዊ አስተዳደርና ሰብአዊ መብት፤ እኩልነትና ፍትህሀሳብን የመግለፅ መብት ጠፋ። ማንም ሰው ስብሰባ ወይም ሰላማዊ ሰልፍ አድርጎ የመቃወሚያ ቀርቶ የአቤቱታ ድምፅ እንዲያሰማ የማይፈቀድለት ሆነ፤ ገበሬው በገዛ ሀገሩ ለባእዳኑ ዘራፊዎች ባርያ ለባእዳን ነፃነታቸውንና ሰብአዊ መብታቸውን ተገፈው፤ በዘራፊዎች እጅ ተጨብጦ በድህነት ወለል ላይ ተጥለውመከረኛ ኑሮ እንደ ባሪያ የሚለፋ ያጣ የነጣ ድሃ ገበሬ፤ ኢትዮጵያ ከብርሃን ወደ ጨለማ ወደ ጨለማ ሰብአዊ መብት፤ እኩልነትና ፍትህ ፍርድ ሰላም ነፃነት፤ የለም ወታደሩም፤ በወታደራዊ ግዳጅ ለአለቆቻቸው የግል ፍላጎታቸው ሲሉ አፈሙዝን ከቶም በወገን ላይ አደረገት ገደሉየገዛ ወገንን የገዛ አገርን ጦቢያን ኢትዮጵያን ገደሉ።

አኝዋኩ፤ ሲዳማው፤ ኦሮሞው፤ አማራው፤ አፋሩ፤ ሀረሪው፤ ትግሬው ጉራጌው፤ ወዘተ…. የጦቢያ ልጆች ሁሉ! ቅን ጎዳና የላቸውም ኢትዮጵያን የሚጎዳ አጥቂ ስራ ይልቁንም ለጉስቁልናዋ፤ ኢትዮጵያን እጅግ ሲፈታተኑ ድርብርብ ስቃይ የአመፅ ፅንስ ብቻ አደረገት!!! ለም ን ልወለድ ?!!!

“የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ”ሰሚ ጆሮ ያለው ይስማ፤የነፃነት ጠላቶች በሰለጠኑባት {“ጦቢያ“} ኢትዮጵያ ለባርነቷ እግዚኦ! አልወለድም ለምን ልወለድ !?

በቀደመው ታሪኩና በብሔራዊ ማንነቱ የሚኩራው የኢትዮጵያ ህዝብ ነው !!!

ገብርኤል ብዙነህ