ግልፅ ደብዳቤ – ለፕሮፊሰር ዶክተር የአርበኞች ግንቦት 7 ሊ/ር ብርሐኑ ነጋ

Print Friendly, PDF & Email

( ግልፅ ደብዳቤ – ለፕሮፊሰር ዶክተር የአርበኞች ግንቦት 7 ሊቀመንበር ብርሐኑ ነጋ, pdf )

ከሁሉ አስቀድሜ የማዕረግ መጠሪያዎትንና በትግሉ ውስጥ ያለወትን የሐላፊት ድርሻ ጠቅሸ ሰላምታየን ባቀርብለወት ስልጣነዎትን ስላልተጋፋሁ ቅርታ እንደማይሰማዎት በመተማመን ነው፡፡
ክቡር ፕ/ዶ/አግ 7/ሊ

አርበኞች ግንቦት 7 የመከፋፈልና የመበተን አደጋ እንደገጠመው ሊቀመንበሩ ለደጋፊዎቹ በይፋ አረጋገጠ!!” በሚል ርዕሰ ለችግሩ መፈጠር ምክነያቶች ናቸው ያሏቸውን በግም ገማ መልክ ኤርትራ ውስጥ ለተካሄደው የደጋፊቸዎት ስብሰባ አንጃ ፈጣሪዎች ያሏችው የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር አመራሮች ባልተገኙበት ያቀረቡትን የግም ገማ ሪፖር ተመልክቸዋለሁ።

በመጀመሪያ እርሰወም ሆኑ ከእርሰዎ ጋር ያሉት መሪዎች ተካሔደ ስለተባለው ጉባኤ የሰጣችሁትን የድል ብሰራት መግለጫና አሁን ደግሞ በእርሰዎ የቀረበውን አርበኞች ግንቦት 7 ተከፈለ ተስነጠቀ አደጋ አጋጠመው……ወዘተ ግም ገማ በመላው ዓለም የሚገኘው ኢትዮጵያዊ ሁሉ የእርሰዎን ድራማና በትግሉ እንቅስቃሴ ላይ ምን ያህል ሲቀልዱበት እንደኖሩ እየተከታተለው ስለሆነ የመጨረሻውን ፍርድም ለመላው ተቃዋሚ ሐይልና ለኢትዮጵያውያኑ መተውን መርጫለሁ፡፡

በዚህ ግልፅ ደብዳቤ ልገልፅለውት የምፈልገው ቢኖር እርሰዎ በዚሁ 8 ዓመታት የትጥቅ ትግል አራማጅና የወያኔ ተቃዋሚ በመምሰል በትግሉና ብታጋዩ ተቃዋሚ ላይ የፈፀሙትን ወንጅል ላስታውሰዎት ነው። ጉባኤውን የጠሩበት ምክንያት የሚመሩት ግንቦት7 በራሱ የቆመ ነፍስ ያለው የወያኔ ተቃዋሚ ድርጀት እንደሆነና ብረት ያነገተ ሰራዊት ያለውት በማስመሰል ባለፉት 3 ዓመታት የሐሰት ፕሮፖጋንዳ ለዲያስፖራው ሲቀልቡት ኖረዋል። ይህ ማብቂ ያልተገኘለት ውሸተዎ ስለተጋለጠ ኪሳራዎትን በዘዴ ለደጋፊወች ለመንገር ሌላ ምክንያት መፍጠር ነበረበወት። ፈልገው ያገኙት ብልሐት አንጃ ተፈጠረና በአንጃው ምክንያት ሰራዊቴ ተበተነ የምትል ዘዴ ፈጠሩ። የሚገርመው በኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባርና በሚጠሉት የአማራ ሕዝብ ላይ ኪሳራዎትን ለማዎራረድ ብለው የለመዱትን የፈጠራ ምክንያት ለመለጠፍ መሞከረዎት ነው። እውነቱን ልንገረዎት እርሰዎ የማያምኑበትን የኢትዮጰያ ስንደቅ አላማ እያስጨበጡ ውሸት ሲቀልቡት ለኖሩት የአማራ ተወላጅ ደጋፊወቸዎት የታጠቀ ጦርም ሆነ የጦርነት ዝግጅት የለኝም ምን ታመጣላችሁ ብለው መርዶውን ልመንገር የጠሩት የእርሰዎ ማታለያ ጉባኤ ነበር።

ወያኔ እውነተኛ ማንነቱ ሲጋለጥ አዘውትሮ የሚጠቀምበን የማጭበርበርና አቅጣጫን የማሳት የክፋት ፖለቲካ እንደሚጠቀም ከእርሰወ በላይ የሚያውቀው አለ ብየ አላስብም። እንዲሕ አይነቱን ሰይጣናዊ የትግል ስልት እርሰወም ከዎያኔ ጋር ውስኪ ጨብጠው ምህላ የፈፀሙበት ስለሆነ ሲጠቀሙበት ለመኖረዎ ለኔ ቀርቶ ለበርካታ ኢትዮጵያውያን ግልፅ ነው። ለዚህ ማሳያ ከጉባኤው ፍፃሜ በሁሏ ስለጉባኤው ውጤታማነት እርሰወና ጓደኞቸውት የሰጣችሁትን የድል ብስራት መግለጫ ሲሽጎደጎድ ተመልክተን ነበር። ከጉባኤው በሁሏ ደግሞ ጉባኤውን ለመጥራት ያጋጠሙ ፈተናወች እንደነበሩ፣ አርበኞች ግንቦት 7 የመከፋፈልና የመበተን አደጋ እንዳጋጠመው በዕርሰዎ የግም ገማ ተቀምጦል። በጠቅላላ ከጉባኤው በፊትም ሆነ በሁሏ የሔዱበት መንገድ ሁሉ እርስ በርሱ የሚጋጭና በሐሰት ላይ የተመሰረተ ጠንካራ ተቃዋሚወችን ሺባ ለማድግረግ የታለመ መሆኑን ከማሳየቱም በላይ የእርሰወን የትግል ታሪካና ተልእኮወትን የፈፀሙበት የዕርሰዎ የብረሃኑ ጉባኤ ለመሆኑ ፍንትው አድርጎ ያሳየ እውነታ ነው እለወታለሁ። የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ከመጀሪያውም ክእርሰዎ ጋር ስላልነብር ጉባኤውን አያውቀውም ተሳታፊም አልነበረም እርሰዎም ይህን እውነት በደንብ ያውቁታል።

ክቡር ፕ/ዶ/የ አግ/ሊ

ኤርትራ ውስጥ ጠራሁት ስላሉት ጉባኤ በትንሹ ከላይ ልግለፅለወት ሞክሬለሁ እስቲ አርበኞች ግንቦት 7 የመከፋፈልና የመበተን አደጋ እንደገጠመው ወደጠቀሷቸው የግም ገማ ምክንያቶቸው በቀጥታ ላምራ፦

በእነ ማአዛው ጌጡ የሚመራ አንጃ ተፈጥሮ ድርጅቱ ለሁለት እንደተከፈለ፣ ነግረውናል

ፕሮፌሰር/ዶክተር/ የአርበኞች ገንቦት 7 ለ/መንበር በእውነት ለመናግ ከልበውት ያስቀመጡት የግም ገማ ነጥብ ነው ብየ ለመናገር እቸገራለሁ ? ለምን ብለው ቢጠይቁኝ አንጃ የሚለውን ቃልና ትርጉሙን ከእርሰወ የግራው ፖለቲካ አራማጅና የኢሕአፓ አፍራሽ በበለጠ ማዛው ጌጡ ቃሉንም ትርጉሙንም ተግባሩንም አያውቀውም። በአርበኞች ግንቦት ሰባት ውስጥ አንጃ ተፈጠረ ብለን እንድናምን ከተገደድን ደግሞ አንጃ ፈጣሪው እርሰዎ እንጅ ማአዛው ጌጡ ሊሆን አችልም። በሌላ በኩል ደግሞ አርበኞች ግንባር የሚለውን ቃል ከሚጠሉት የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር መጠሪያ ስያሜው ውስጥ ነጥለው በማውጣት ግንቦት ሰባት ከተባለችው ማሳበቂያ ድርጀተወት ስያሜ ጋር በመለጠፍ በሻቢያ በኩል ስጦታ ተበረከተለዎትና ለ3 አመታት ያህል አታለሉባት። ማአዛው ጌጡ በራሱ ድርጀት ላይ አንጃ የሚፈጥርበት ምክንያት የለም። ሌላው ደግሞ በሕጋዊ መንገድ ከኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ጋር ምንም አይነት ግንኙት አልነበረወትም እንዲኖረዎት የሚያድርግ ሞራልም ሆነ ስነምግባር የለዎትም ይህን በሚገባ እያወቁ ያላዩትንና አንድም ቀን እንኳን የማያውቁትን ሰራዊት እንደነበረዎት አስመስለው ለጠሯቸው የጉባኤ ተሳታፊወች አንጃ ተፈጠረ ጦሩ ከዳን በማለት ለማሳመን መሞከረዎት የእርሰወን አታላይነት ለማያውቁትና የተልዕኮዎትን መጨረሻ ነጥብ ላላወቁ ደጋፊዎቸዎት ይጠቅም ካልሆነ በስተቀር ምክንያተዎት ተቀባይነት የለውም። ዛሬ ማንንም ሊያታልሉ አይችሉምና እርሰዎም ሆኑ ድርጅተዎት ግንቦት 7 ድርጅት እንዳልሆናችሁ እራሰዎ ተናግረዋል እኮ። መተኪያ የሌለውን ሕይወቱን ለኢትዮጵያ አገሩ ደህንነት የሚሰጥ ተዋጊ አርበኛ ቀርቶ እንደ ድርጀትም ድርጅት አይደላችሁምና አይቸገሩ።

በግም ገማወት ላይ ሴራውን የጀመረው ዘመነ ካሴ እንደሆነና በኢንተርኔት አንመራም የሚል አቋም ያራምድ እንደነበር ጠቅሰዋል።

እርሰዎ የማይዋሹት የለምና እስቲ ጥያቄዎችን እንዳቀርብለወት ይፍቀዱልኝ ? ለመሆኑ ዘመነ ካሴ የሚቀርበው ለማን ነው ? የፊሺካው ተነፋ ዘምቻ የግንቦት 7 ሕዝባዊ ስራዊት መስራች አልነበር እንዴ ? በየት አለፎ ነው የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር አንጃ ጥንስስ ፈጣሪ ያደረጉት ? ለመሆኑ ከሱ ጋር ወደ ኤርትራ ያስገባችሗቸውን ወገኖች እንዴት አድርጋችሁ እንደበተናችሗቸው ለጉባኤው ተሳታፊውች ሪፖርት ለምን አላቀረቡም ? አለሁበት ለማለት ማሰልጠኛ ከፈቻለሁ፤ ጦር አለኝ፣ በዚህ ቦታ ዘመቻ ውያለሁ፤ወያኔን ገድያለሁ ማረኬለሁ ድል በድል ተጎናፀፍኩ በማለት ያላደረጉትን ሲሰብኩና በኢሳት ሲያሰብኩ አልነበር እንዴ ? በትግል ታሪከወትም ሆነ ልምደወት ወያኔን የሚቃወም አጀንዳ እንደለለዎት በግሃድ የታወቀ አይደለም እንዴ? ታጋዮችንና ብሶተኛውን የኢትዮጵያዊያ ሕዝብ ሲያታልሉና በደል ሲፈፅሙበት መረጃ ለወያኔ ሲያቀብሉ መኖረወትን እንዴት እረሱት ? በእርሰዎ የውሸት ጦርነት ዘመቻ ሳበያ በበርካታ ወገኖች ላይ ወያኔ የፈፀመውን ወንጀል ለምን የጉባኤው ተሳታፊዎች አልተዎያዩበትም ? በጭፍኑ ይቅርታ አድርጉልኝ ከማለት ይልቅ ለይቅርታ ጥያቄዎት ምክንያቱን ለጉባኤው ግልፅ ሪፖረት ለምን አላቀረቡም ?

ዘመነ ካሴ አማራ ነው ብለው እንቅልፍ ስለነሳዎት ብቻ የሱን ስም ለማጠላሸት አንጃ ተፈጥሮል በሚል ማስመሰያ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባርን ለመበታተን የሔዱበትን ረጅም መንገድ ለማድበስበስ ለምን ይሞክራሉ ? የእርሰዎ አንጃ ተፈጠረ ግም ገማ ዕራሰዎት ያጠለቁትን ወያኔዊ ጭብል ገላልጦ የሚያሳይ እንጅ በየትኛውም መስፈርት አንጃ ፈጣሪ ያሏቸውን ዎገኖች ድክመት የሚገልፅ አይደለምና አይጨነቁ። ብረሐኑ ነጋ አይመራንም የተባሉበት ምክንያት እኮ ከዚህ በላይ ላማሳየት እንደሞከርኩት የወያኔ ደጋፊ እንጅ ተቃዋሚ አለመሆነወትን በተለያዩ ወቅቶች ባደረጓቸው ንግግሮቸዎት ዕራሰዎ ስላረጋገጡልን ነው። መቸም ቢሆን የወያኔው ሕገ-መንግስት ደጋፊ የመለስና የታምራት የብርጭቆ ውስኪ ጓደኛ የነ ሌንጭና አረጋዊ በረሔ የቅርብ አማካሪ መሆነዎትን አይክዱምና ተቃዋሚውን ያውም የትጥቅ ትግል አራማጁን ሊመሩት ቀርቶ ሊመለከቱት ሞራሉ የለወትም ቢሉወትስ ለምን ይከፋዎታል። በሻቢያ ጫና እንደሙጫ ተጣበቄ መሰለል አለብኝ ብለው ለምን ይከራከራሉ።

ችግሩን በተለያየ ጊዜ በሺምግልና ለመፍታት ጥረት ቢደረግም ሳይሳካ መቅረቱን፤ ነግረውናል

አጀብ ነው የሚያሰኘው ! አንጃ ተፈጠረ እያሉ እርቅ አለ እንዴ ? አንጃው የተፈጠረበት ምክንያት ሳይታወቅ እንዴት ያለ ሺማግሌ ተገኘ፡ ይኸ ሁሉ ፈጠራ የእርሰውን ተልኮ መሳካት ይገልፅ ካልሆነ በስተቀር የኢትዮጰያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር እርሰዎን የሚያውቀዎት የወያኔ ጉዳይ አስፈፃፊና ተንኮለኛ ስላይ መሆነዎትን ነው። ስለዚህ ከእርሰዎ ጋር እርቅ ሳይሁን ሊያጠፉት የተጣበቁ ሙጫ ስለሆኑ ከላው ላይ መንጭቆ መጣል ስለነበረበት ካሰናበተዎት ቆይቶል እና አይድከሙ ! በዎቅቱ ሺማግሌም መግባት አላስፈልገውም ነበር። ለዚህም እኮ ነው የውሸት ከረጢተወት ተፈቶ ጉደዎት የፈላው። ለፈፀሙት ወንጀል ደግሞ የጊዜ መስፈሪያ እናበጅለታለን ጊዜ ለኩልክሙ ይላል ግዕዝ። ይህነን እውነት ግን ለሰበሰቡት ደጋፊዎቸዎት መንገር ነበረበዎት እለወታለሁ። ይህንን ሁሉ ጉድ ሳይናዘዙ ደጋፈዎቸዎን ይቅርታ መጠየቁ ጮሌነተውን ከመግለፅ በስተቀር በውሸት ሲጋልቧቸው ለኖሩት ደጋፊዎቸወና ትግሉን ለመግደል ያደረጉትን ዙሪያ ጥምትም ሴራ የሚደብቁት ተገባር አይደለምና መዝናናት የለበወትም።

ክቡር ፕ/ዶ/የ አግ 7/ሊ/መ ቡርሐኑ ነጋ የግም ገማ ሪፖርታቸውን ለጉባኤው ተሳታፊወች በሚስጥራዊ ገለፃቸው እንዲህ ይላሉ፤-

– አንጃው በፈጠረው ችግር ሠራዊቱ በቡድንና በግል ወደተለያዩ አካባቢ መበተኑን እና ይህንንም ለማስተካከል የኤርትራ መንግሥት ባደረገው ድጋፍ ከቀሩት በጣም በጣት የሚቆጠሩ የሠራዊት አባላት ጋር ግምገማ መደረጉን፣ በግምገማውም

• መአዛው ጌጡ ስልጣኑን ከብርሃኑ ነጋ ለመቀማት ያሴር እንደነበር ማመኑን፣

• አሰፋ ማሩ (አመነሸዋ) እና ኑርጀባ የሚዋዥቅ አቋም እንደነበራቸው፣

• አንድ አመራር ሊጠፋ ሲል በመያዙ እስከ አሁን መታሰሩን ገልጿል፡፡ (ይህ ግለሰብ በሻዕቢያ በደረሰበት ከፍተኛ ድብደባ ህይወቱ በአደጋ ላይ መሆኑ ተረጋግጧል፡፡)

ክቡር ፕ/ዶ/የ አግ7/ለ/መ፡

አንጃ እያሉ ስለሚጠቀሙበት ቃላት ትርጉም ከእርሰዎ የበለጠ አንጃ ፈጠሩ የሚሉቸው ግለሰቦች አያውቁትምና በህግ አምላክ ያቁሙ እንዳልለውት እርሰዎም ሁኑ የሚደግፉት ወያኔ ህግ የሚባል ስለማታውቁ ሰውን በማያውቀው ቋንቋና ፅንሰ ሐሳብ መዎንጀል ጥርሳችሁን ንቅላችሁ ያደጋችሁበት አጭበርባሪነት ስለሆን ከምትፈፅሙት ዎንጀል አትመለሱምና በሐያሉ ሕዝባች ክንድ እስክትቀጡ ድረሱ እንድሁ ቀጥሉበት። በግለሰቦቹ ምክንያት ተበተነ ለሚሉት ሰራዊት ግን እርሰዎና መሰሎቸዎት የትጥቅ ትግሉን ለማዳከም ተልኮ ሰንቃችሁ ለ3ት አመታት የሰራችሁትና ትንሺም ቢሆን የተሳካላችሁ ስለሆነ እኔን አያስደንቀኝም።

ተበተነ የሚሉት ስራዊት በእናንተ የውሺት ድለላ ከተለያዩ ዓለማት ያስገባችሗቸው ዎገኖች ከገቡ በሁላ እናንተ የነገራችሗቸው ሌላ የጠበቃቸው ሌላ በመሆኑ የእናንትን አቋም ጥሩ አድርገው በመረዳታቸው ተበተኑ። ምንም እንኳን ቅጥረኛ ወታደር ገዝታችሁ ጉዳት ብትፈፅሙባቸውም ከእናንተና ከወያኔ ሰላዮች ግድያ ለማምለጥ ስለሆነ የጠፉት የእርሰዎ እንቶ ፎንቶ ተነቅቶበወታልና ማቆሙ መልካም ነው እለዎታለሁ። ይህ እኮ የተበላ ቁቤ ነው ሌላ ዘዴ ቢመርጡ አይሻልም እንዴ ? የመውጣት እድሉ ገጥሟቸው ከወጡ በሁላ በተለያዩ ሚዲያዎች የገለፁት በመሆኑ ተጠያቂው እርሰዎ እንጅ አንጃ ፈጣሪ ያሉቸው ግለሰቦች አይደሉም። ድምፃቸውን ከፍ አድርገው እርሰዎንና ጓደኞቸዎትን ተጠያቂ እደሆቻችሁ ምስክርነታቸውን ስለሰጡበት በዚህ በኩልም የግም ገማ ሪፖርተዎት “ ጅራፍ እራሱ ገርፎ እራሱ ይጮሃል” የተባለውን ምሳሌዊ አነጋገር ከማስታወሱም በላይ ወያኔ ወያኔ ይሸታል። ወያኔ ገድሎ ልቅሶ ይደርሳል እኮ። እርሰዎም የጉባኤ ተሳታፊ ያሏቸውን ደጋፊዎችዎትን የናቋቸው ይመስለኛል፤ ያልሰሙ ያላነበቡ አስመስለው አይናቸውን ጨፍነው ጆሮቸውን ደፍነው እንዲቀበሉዎት ይፈለጋሉ እንዴ ያሳዝናል ።

ማአዛው ጌጡ ስልጣኑን ከብርሐኑ ነጋ ለመቀማት ያሴር እንደነበር ማመኑን፡ ይሉናል ዶ/ር ብርሐኑ

በመጀመሪያ ደረጃ ወያኔን በጦርነት ለማውረድ እርሰዎ አጀንዳ የለወትም፡ በኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ደንብና ፕሮግራም መሰረት ወያኔን በሚገባው ቋንቋ በማናገር ከህዝባችን ትከሻ ላይ ማውረድ እንጅ ስልጣን በህዝባችን ባለቤትነት ተረጋግጦ ለሚፈልገው የሚሰጠው ሕዝቡ ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ትግልም ለስልጣን ባለቤትነት አይደለም። በጦርሜዳ ፍልሚያው በኩል ያለውን ስልጣን ኮሆነ ደግሞ በመጀመሪያ የተዋጊው ሰራዊት አባላት ለአባለነት የሚመዘገቡበትን መመሪያ አሟልቶ የተመዘገበና ጠንካራ ወታደራዊ ስነ-ምግባር ያለው የጎበዝ አለቃ ወይም ኮማንደር ሆኖ ሊሾም ይችላል። እኔ እስከማውቀው ድረስ እርሰዎ የተዋጊው ሰራዊት አባል አይደሉም ውጊያ ውስጥ መዋል ቀርቶ ሰምተው ስለማያውቁ አርበኛም አይደሉም ጠንካራ ወታደራዊ ስነ-ምግባርም የለወትም፡ ታዲያ የትኛውን ስልጣን ነው ማዛው ጌጡ ሊቀማወት አሲሮ ስህተቱን አውቆ ይቅርታ የጠየቀወት ? ስለየትኛው ስልጣን ነው የሚያወሩት ? አገር አድን የሚባል ግሩፕ እደመሰረቱ ከወደ አሚሪካ በኩል ይነገራል ያ ከሆነ ደግሞ ሌንጮንና አረጋዊ በረሔን መጠርጠሩ ይሻል እንደሆነ እጅ በጦርሜዳ ያለ ስልጣንማ የጦር ሜዳ ሞያን የሚጠይቅ ነው። ተጀምሮ እስኪጨረስ የዕርሰው ሕልም የኸው የስልጣን ልክፍት ስለሆነ 90 ድግሪ ያዞረዎታል። ቤጤዎቸዎን እየፈለጉ ከነሱ ጋር ሆነው የተለከፉበትን በሺታ ያስታሙ በእውነት ነው የምለዎት። ማዛው ጌጡን ለቀቅ ያድርጉት።

ማፈሪያዎትን አያውቁምና ለደጋፊዎቸው የተሳሳተ መልዕክት አይሰጣቸው ውነት ውነት እለወታለሁ ትልቅ ወንጀል ነው። አሰፋ ማሩ፤ ኑርጀባ አሰፋም የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር አባሎችና ጠንካራ የጎበዝ አለቆች ወይም ኮማንደሮች እንጅ እርሰዎ በሚሰቃዩበት በሺታ ገብተው ለመሰቃየት ስላልፈቀዱ በእርሰው ሊወረፉ አይገባም። በርግጥ ነው ዋናው የእርሰዎ ተልዕኮ ስንት ጀግኖች የወደቁበትን የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ለማጥፋት መሆኑ ጠፍቶኝ እንዳይመስልለዎት። አንጃ ፈጠሩ የሚሏቸውም ኮማንደሮች ግንባሩን ከእንደሰዎ ካለ ሰላይና የሁለት ዓለም ሰው የደገሱለትን ጥፋት የመከላከል ሐላፊነት ስላለባቸው በግንባሩ ዙሪያ ዝር እንዳይሉ መከላከላቸውያስመሰግናቸዋል እንጅ የሚያስወቅሳቸው አይደለም እለወታለሁ።

አንድ የግንባሩ አመራር አባልም ሊጠፋ ሲል በሻቢያ ተይዞ ተደብድቦ ለሕይወቱ አስጊ ስለሆን በእስርቤት እንደሚገኝ ጠቁመውናል፡

ክቡርነተዎ፡ ምን ታየዎት! ለጉባኤው ተሳታፊወች እንዲህ ዓይነቱን አስደንጋጨ ሪፖርት የነገሯቸው ደፋር ነዎት ማለት ነው፤ ሻቢያ በተወካዮቹ አማካኘነት ከግም ገማ ሪፖርቱ ስብሰባ ገብቶ ስምቶዎታል እኮ? “ አያ በሬ ሆይ ሳሩን አየህና ገደሉን ሳታይ ” እንዳይሆንበዎት፡

ክቡርነተዎ ይን ያህል ደፋር ከሆኑማ ትንሺ ጥያቀዎችን ልጠይቀዎት ? እርሰዎን የግንባሩ መሪ ያደረገዎት ማን ነበር? የጦሩ መሪ ሆነው ከተሰየሙ ጅምሮ በሰራዊት ላይ የሚታየውን ጥንካሬም ሆነ ድክመት ሻቢያ ነው እንዴ ሪፖርት የሚያቀርብለዎት? በኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ልዩ ልዩ ሐላፊዎች (ከማንደሮች) ላይ ያነጣጠረ ትግል ማድረግ ለምን ፈለጉ?አንድ ግለሰብ በሻቢያ መታሰሩን፤ መደብደቡን እርሰዎ እንዴት አወቁ ? በነካ አፈወት ስለ ግንቦት 7 ህዝባዊ ጦር አባላት መበተን መደብደብ፤ መታሰር፤ መገደል ዝርዝር ሪፖርት ለግንቦት 7 1ኛ ጉባኤ ተሳታፊወች ለምን አላቀረቡም? ኮማንደሮቹን ጉባኤው እንዳይጠራና እንዳይሳካ ብዙ ጥረት አድርጎል ብለውናል። ከማያወቁት የደርጅተዎት ጉባኤ ላይ አንገኘም ማለታቸው ወንጀላቸው ምኑ ላይ ነው? ለነገሩማ እርሰዎ በጥናትና በምርምር የሚመሰርቷቸው ተቃዋሚ ድርጅቶች በአንድ ቀን ተገንብተው ሲፈርሱም የ3ቀን እድሜ አይሞላቸውም ለመሆኑ ከሞላ አስገዶም ጋር በረጅሙ ጥናትና ምርምር ግኝተወት እንዳይፈርሰ ሆኖ የተገነባው ግንባር የት ደረሰ ? ሌላው ቀርቶ የአካዳሚ እውቀተዎትን ጥያቄ ውስጥ የከተተ አይመስለወትም ? ፕሮፊስሮች ፣ዶግተሮች… የሚናግሩትም ሆነ የሚፅፉት አለማቀፋዊና እውነትነት ያለው ነው። መቸም ገበሬው ሞላ አስገዶም ይበልጠወታል ለማለት አልደፍርም ነገር ግን የተናገረውን አዳምጫለሁ እርሰዎን በተመለከተ ለቀረበለት ጥያቄ መልስ ሲሰጥ ፕሮፌሰሩ እልም ያሉ ውሸታም ናቸው ዓለ እኮ። ያውም በዝምድና ከተመዘነ እሱና እርሰዎ የህገመንግስቱ ተቀባይ ያዎ የወያኔ ቤተሰቦች ናችሁ።

ተመልሰው ደግሞ በእርሰዎ ጥንካሬ ጉባኤው ተጠርቶ ስብሰባውን በተሳካ ሁኔታ አካሔደናል እያሉ ነው። ኤርትራ ውስጥ ጉባኤ የጠሩት እርሰዎ ግንቦት ሰባት የሚሉትንና በሁሏ ደግሞ ድርጅት አይደለም ያሉትን ትርጉም የለሺ ስያሜ የመጀመሪያ ጉባኤውን አከናወን ነው ያሉት፡ ከነገራችን ለይ እርሰዎም ሆኑ ግንቦት 7 ሰባት የሚሉት ንቅናቄዎት ህይዎታችሁ ያለው ኢሳት ውስጥ እንጅ መሬት ላይ እማ የላችሁም እኮ እርሰዎም ደጋፊዎቸዎትም በደንብ ታውቁታላችሁ። የሚቀጥለውን ማሳያ እንደምሳሌ አድርጌ በትንሹ ላመላክተዎት። በቅርቡ እርሰዎንና ጓደኞቸዎትን አምነው የኢሳትን ሌት ተቀን የክትት ዘመቻ አዋጅ አዳምጠው ትግል አለ ብለው ድርጅተዎት ግንቦት 7ን እንደደርጅት በራሱ የቆም ሕይወት ያለው መስሏቸው የሞቀ ቤታቸውን አፍርሰው ልጆቻቸውን ደፍተው ለትግሉ ቅድድሚያ ሰጥተው ኤርትራ የገቡትን የዋሆች፦

1ኛ. ታጋይ አርበኛ ሻለቃ መሳፍንት

2ኛ. ታጋይ አርበኛ ተስፋ ላቀው

3ኛ. ታጋይ አረበኛ ይገዙ አጣናው

4ኛ. ታጋይ አርበኛ ዳኜ አያሌውን ……..ወዘተ ማን ገደላቸው ?

ለግንቦት 7ቱ መጀመሪያ ጉባኤ ተሳታፊወች ሪፖርቱን አቅርበው ውይይት ተካሔዶበታል ? ታዲያ እዲሕ አይነቱን ጉድ እና ወንጀል አስቀምጠው የትጥቅ ትግሉን ለማዳፈን ከወያኔ የተሰጠወትን ተልዕኮ በማገባደድ አስመራ ውስጥ ጉባኤ መጥራትና የተሳሳተ መልክት ለጉባይተኛው ታዳሚ ማቀበልን መረጡ እኮ።

ክቡር ዶ/ር ብርሐኑ እንዲህ ይሉናል፦

በዚህ ጉባዔ ላይ ከሠራዊቱ ውስጥ 50 የማይሞሉ አባላት እንደሚሳተፉ እነርሱም በአንጃው የተለያየ በደል (እስር፣ ግርፋት፣ ከባድ የጉልበት ሥራ ……) የደረሰባቸው በመሆኑ የተጎሳቆሉ መሆኑን፣

ምን ነካዎት ስለየትኛው ሰራዊት ነው የሚናገሩት እርሰዎን አምነው የተቀመጡትን ከሆነ እንደሚሳተፉ የሰብሰባውን ቀኑንም ሰዓቱንም ነግራችሗቸው ይጠባበቁ ነበር። ነገር ግን ቁጥሩን እርሰዎ እዳጋነኑት ያህል ጉባኤ የሚሳትፍ ወታደር እንደሌለውት ብናውቅም እናንተን አምነው ገብተው ከተበተኑት የቀሩ በረሐላይ ጠያቂ አጥተው ከ10 የማይበልጡ ውንድሞቻችን ነበሩ። ከነዚህ ውስጥ ከጉባኤው ላይ ተገኝተው ጉዳታቸውን ለመናገር እንደተዘጋጁ ስላዎቃችሁ የገለፃችሁላቸውን የስብሰባ ቦታና ቀን በመለወጥ ሸዎዳችሗቸው በድርጊታቸሁ ተናደው ቦታወንና ቀኑን አፈላልገው ለመሳተፍ ከፍተኛ ጥረት አድርገው ለአደጋ ስለተጋለጡ ከላይ ስማቸው ከተጠቀሱት ታጋዮች ውስጥ 3ቱ ሕይወታቸው ያለፈው በዚህ ምክነያት ነው። ከዚህ ውጭ ድብደባም በሉት ግድያ የተፈፀመው እርሰዎ በፈጠሩት የውሸት ክምር የተናደዱት ጥቂት የግንቦት 7 አባሎች ከርሰዎ ጋር በመጋጨታቸው ቅጥረኛ ውታደሮችን በገንዘብ እየገዙ የሚያስደበድቡትም የሚያስገድሉትም የሚያሳስሩትም እርሰዎ ነወት እኮ፡ የማንነ እከክ ወደማን ለከክ ያደርጋሉ። የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ስራዊት ከእርሰዎ ጋር ግንኙነት ስለሌለው ጉባኤውን ቀርቶ እሰወንም ስለማያውቀወት ከምነወትም ደርሶ አያውቅም የተናደዱትም ገብተው ባለመፈትፈተዎት ምክንያት እኮ ነው።

ክቡር ዶ/ር ስለ ኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር የሚከተለውን የግም ገማ ሪፖርታቸውን እንዲህ ይላሉ፡

መአዛው ጌጡ እና ቡድኑ ዘራፊና በህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ተሳታፊ መሆኑን ለዚህ የኤርትራ መንግሥት የተደበቁ በርካታ መሣሪያዎችና ገንዘብ እንዳገኘባቸውና በምርመራ ላይ መሆኑን፤

የዚህ ሁሉ ችግር ዋና መነሻው የተበላሸ የአሰራር ባህልና ልምድ ካለው ጋር ራሱን የአማራ ወኪል ነኝ ከሚለው የሽፍቶች ስብስብ ከሆነው የአርበኞች ግንባር ጋር የተደረገው ውህደትና ውህደቱን ተከትሎ የአመራር ቦታ በአቅም ሳይሆን በኮታ መደልደሉ መሆኑን የገለፀው ብርሃኑ ነጋ በዚህ ለፈፀምነው ስህተት ይቅርታ እንጠይቃለን በማለት መሬት ላይ በሌለ የሃሰት ወሬ ሲነዱ የከረሙት ከተለያዩ ሃገራት ወደ አስመራ የገቡት የድርጅቱ አባላት ኤርትራ ውስጥ በሚያጋጥማቸው ያልጠበቁት ሁኔታ እንዳይደናገጡ ከወዲሁ ለማረጋጋት ጥረት በማድረግ ለጉባኤው እንዲዘጋጁ ማድረጉን ለማወቅ ተችሏል፡፡

ክቡር ፕ/ዶ/የአግ/ሊ/መ

በመጀመሪያ ደረጃ የግንባሩን ልዩ ልዩ አመራሮች ዒላማ ያደረገ ውንጀላና ስም ማጥፋት የጀመሩት ዛሬ አይደለም ቅንጅት የተባለውን የፖለቲካ ድርጅ አፍርሰው በውጭ ሐገር ያሉትን ተቃዋሚዎች ለማፍረስ ወያኔ የሰጠወትን ተልኮ ለመፈፀም በአጀንዳወት ውስጥ መጀመሪያ ከመዘገቡት ድርጅቶ ውስጥ የትጥቅ ትግል በማድረግ ላይ ባለው የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ላይ ነበር። የመጀመሪያው አቀራረበውት የትጥቅ ትግል አራማጅ መስለው በመታይት የተለያዮ ተላላኪወችወትንና አንዳንድ የዋሕ የሆኑ የግንባሩን መሪወች በመስበክ እደሙጫ የሚጣበቁበት መንገድ ለማመቻቸት ሞክረዋል፡፡ ከአታለሏቸው የግንባሩ መሪወች ውስጥ ማዛው ጌጡ አንዱ ነው። ዛሬ ተልዕኮዎትን ሲጨርሱ የሐሰት ስም ማጥፋት ዘመቻዎትን ከፈቱበት። በነገራች ላይ ማዛው ጌጡን ከ 3ቀን የበለጠ ያዩትና የሚያውቁት አይደለም። እርሰዎ ከላይ የለጠፉበት የሰውና የመሳራሪያ ነጋዴ ነው ልጠፋዎት ከቶውንም አይጠጋውም እርሰዎ ለዋቢነት የጠሩት ሻቢያ ማዛውን ጥሩ አድርጎ ያውቀዋል። በከንቱ ደከሙ እንጅ ሻቢያ በመሬቱ ላይ ማዘው ጌጡ እንዲህ አይነቱን የወያኔ ተግባር የሚፈፅም መሆኑን እያወቀ እንደእርሰዎ ካለ በሰላይነት ከተካነ ወያኔ ጋር አያገናኘውም ነበር። ይሕ ስም አጠፊነተዎ የእርሰዎ ተልዕኮዎ ስለሆነ የትጥቅ ትግል የሚመሩ መሪወችን ቀርቶ የሲቪል ተቃዋሚ መሪወችን ሁሉ ነው። በእርሰዎና በወያኔ ስም ያልተለጠፈበት ተቃዋሚ አለ እንዴ? ላስታውሰዎት ጀኔራል ከማል፣ መንግስቱ ወ/ስላሴ፤ ዘመነ ካሳ፤ ኑር ጀበ አሰፋ አሰፋ ማሩ ፤ ሙሴ ተገኘ፤ ኤልያስ ክፍሌ፤ደምስ በለጠ፣ ሞላ አስገዶም፤ ጁዋር መሐመድ……ወዘተ ባጠቃላይ የእርሰወን ወያኔነት ያዎቁበወትንና ለፉገራ ፖለቲካዎት ያልተበገሩት ሁሉ ይለጥፉባቸዋል ያሰድቧቸዋል ተሳዳቢዎችንም በፌስቡክ፤ በፓል ቶክ ቀጥረዋል። ዋና ዓላማዎትም ተቃዋሚዎችን ለመበተን አመራሩን በማዋከብ ድርጅቱን ማፍረስና ከወያኔ ቢዝነስ ጋር መጋራት ነው። ስለዚህ በግም ገማ ሪፖርተወት ውስጥ ስለማዛው ጌጡ ያቀረቡት ፉገራ ወያኔ ሲለው የኖረ የተበላ ቁቤ ስለሆነ ማዛው ጌጡን አይጠጋውምና አልቀናወትም ከስረዋል።

ፕ/ዶ/የአግ 7/ሊ/መ ስለ ኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር የሚከተለውን ግም ገማ አቅርበዋል፤ የዚህ ሁሉ ችግር ዋና መነሻው የተበላሸ የአሰራር ባህልና ልምድ ካለው ጋር ራሱን የአማራ ወኪል ነኝ ከሚለው የሽፍቶች ስብስብ ከሆነው የአርበኞች ግንባር ጋር የተደረገው ውህደትና ውህደቱን ተከትሎ የአመራር ቦታ በአቅም ሳይሆን በኮታ መደልደሉ መሆኑን የገለፀው ብርሃኑ ነጋ በዚህ ለፈፀምነው ስህተት ይቅርታ እንጠይቃለን ።

ክቡር ፕ/ዶ/የአግሊ/መ

የዚህንን ግም ገማ ሪፖርተዎን ጊዜአቸውን አባክነው ላዳመጡዎት ደጋፊዎቸዎ በጣም አዘንኩላቸው። ምነው ቀለሉ ? ጭራሺ ተዋረዱ እኮ ፕሮፊሰር ዶክተር የጦር መሪ ማለት እንደዚ ያለ ነው እንዴ ምሁሩም ወታደራዊ መሪውም በእርሰዎ የጥናት ግም ገማ ሪፖርት አፈረ እኮ። ደጋፊዎቸዎትነና ኢትዮጵያዎያንን የውሸት ትጥቅ ትግል ገባሁ ማሰልጠኛ ከፈትኩ፤በወያኔ ላይ የጦርነት ፊሽካ ነፋሁ በመላው አገሪቱ ሰራዊት አሰለፍኩ አዲስ አበባን ለመቆጣጠር እንጦጦ ቀርበናል….. እየተባለ ለ3 ዓመታት ያላቋረጠ የፈጠራ ውሸት አራግበዋል።

ግንቦት 7 የሚሉትን የፉገራ ድርጅተዎ በራሱ የቆመ ድርጅታዊ ሕይወት ያለው አስመስለው በደጋፊወቸዎ ላይ ቢዝነስ መሳይ ሲመቱባቸው መኖረወትን ሊደብቁት አይችሉም። የሺፍቶቹም ግንባር ለውሸተዎ ማጣቀሻ ለመሆን ስላልፈለገ በራሰዎ ቅሌት ደጋፊወቸዎን ጠርተው ያለዎትን ጦር ማሳየት ባለመቻለዎት ሊደብቁት የማይችሉት እውነት ጉሮሮዎትን አነቀዎትና ወያኔዊ ጭምብለዎት ተጋለጠ። ታዲያ ምን ነካዎት አበዱ እንዴ መቸ ነው ከአርበኞች ግንባራ ጋር ውህደት የፈጠሩት? በህልመዎት ነው በዎነዎት ? ወደሺፍቶቹ የመጣችሁት በመጀመሪያ የእርሰዎ ተላላኪወች ቀጥለው እርሰዎ እራሰዎት እኮ ነዎት የመጡብን አይደለም እንዴ?

ሳይሳካላችሁ ቢቀርም እርሰዎና መሰሎቸዎ የአማራ ተወካይ ሽፍታ ልትሆኑ ነበር ማለት ነው የመጣችሁት? ከእርሰወ ቤት እውነት አይጠፋም ብየ ነው የጠየኩዎት ሻቢያ እንደስጦታ በሸለመዎት አርበኝነት ስማችን ላይ እንደሙጫ ከኛ ከሺፍቶቹ ጋር ለመጣበቅ ለምን ደከሙ ?። እንደ እርሰዎ ያለው ወያኔ ሐፍረት የሚባል አያውቅም እንጅ በቁመዎት ሞተዋልና አርፈው ይቀመጡ። በእርሰዎ አባባል የአማራ ወኪል ነኝ ከሚለውና ከሚጠሉት የሺፍቶች ስብስብ ከሆነው የአርበኞች ግንባር ጋር ውሕደት ቀርቶ መልካም ግንኙነት የሚባል እደሌለዎት እያወቁ ለጉባኤየዎት ተሳታፊወች ውህደት እንደነበረዎት በማስመሰል በሪፖርተዎት ላይ ይቅርታ አድርጉልኝ በማለት ማብቂ በሌለው ውሸተወት የሚያዋክቧቸውን ደጋፊዎቸዎን ለማታለል ለምን ፈለጉ?። ከዚህ ላይ መጠርጠር አለብን በጤናወት አይመስሉኝም።

ከቡር ፕ/ዶ/የአገ 7/ሊ/መ

መቸም እንደሰዎ ላለ ተመራማሪና አዋቂ የግም ገማ ሪፖርት አቀራረብ እንዲህ ነው እዲያ ነው ብሎ መንገር ከባድ ነው። ነገር ግን እንኳን እኔ ቀርቶ ፈደል የመቁጠር እድሉን ያለገጠማቸው ዘመዶቸ ስለ አንድ ጉዳይ ለማስረዳት ሲቀርቡ የመልክቱን መሰረታዊ ጉዳይ በቃልም ሆነ በምልክት በቀጥታ በማመላከት ነው። አይለውጡም፣ አያስረዝሙም፣ አያሳጥሩም። እርሰዎ ግን ፈጣሪዎት ወያኔ የሐገርና የሕዝብ ጠላት መሆኑን አምኖ ተራራ መስረቁን፤ ሕንፃ መደበቁን፤ድልድይ ማፍረሱን፤ ካዝና ማራገፉን…ወዘተ አምኖ ከልብ ልታደስ ነው በሚልበት ወቀት እርሰዎ ግን እስካሁን ድረስ ከዚያው ነዎት በኔ እይታ ሰነፍ ወያኔ ያደርገዎታል። በዎስጥም ሆነ በውጭ በኢትዮጰያውያንና በተቃዋሚ ድርጅቶች ላይ የሚፈፅሙት ያረጀ ያፈጀ ፖለቲካና ወያኔዊ አታላይነትን ጠብርግፍ አድርገው ትተው ለመታደስ ባለመዎሰነዎት ይኸውና በተቃዋሚው ጎራ ላይ የከፋ ወንጀል እየፈፀሙ ነው።

እንደሚያውቁት እርሰዎ ያለተዋዋሉት ድርጅት የለም ሳይውል ሳያድር ያላፈረሱት ድርጅትም ሆነ ሕዝባዊ ማህበር የለም እኮ ለመዘርዘር ብሞክር ወረቀት ስለማይበቃኝ መተውን መርጫለሁ። እንዲህ አይነቱን ከፍተኛ አፍራሺነወትንና ማን አለብኘነትዎን እንዲተው ጠጋ ብሎ የሚመክረወት ሁነኛ ዘመድ አዝማድም ያለውት አልመሰለኝም። የተለከፉበት ስለጣን በሚባለው በሺታ። ቀዳሚው የአገርና የሕዝብ ደሕንነት ነውና በአሁኑ ወቅት ያለው የትግል ባህሪይ የሰዎን በሺታ ለማከም የሚችል አይመስለኝም።ስለዚህ ትግሉ አይመጥነዎትም። በማጭበርበር የሚገኝ ስልጣን እንደወያኔ አገርና ሕዝብ ያጠፋ ካልሆነ በሰተቀር የሚጠቅመወት ነገር የለም። እርሰው ከእንግዲህ በሁላ ሊታመኑ የሚችሉበት ፖለቲካዊ ሞራል የለወትም አርፈው ቢቀመጡ ከሌላ ወንጀል ይድናሉ፡፡ የሚመኩበት ወያኔም በቁልቁለቱ ሸርተቴ እየነጎደ ነው። ተግባባን ፕሮፌሰር በመጨረሻም ልገልፅልወት የምፈልገው የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ገና ከጅምሩ ወያኔን ከተሰቀለበት ማማ ለማውረድ በሚገባው ቋንቋ በማናገር ብቻ ነው ብለው ባመኑት ወልቃይት ጠገዴ ውስት ከፋኝ በሚል መጠሪያ ተመስርተው በሁላ ላይ በመላው ሐገሪቱ ተስፋፍተው ለሐገራቸውና ለወገናቸው ነፃነት መተኪያ የማይገይለትን ሕይወታቸውን ገበረው የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞችን ፈጥረው ዛሬም ወያኔን በመፋልም ላይ ያሉ የሐገሪቱ የቁርጥ ቀን ልጆች ናቸው።

እርሰዎ ወደ አርበኞቹ ጎራ ብቅ ብለው እንደፎከሩት ድርጅቱን ለማፍረስ እረጅም መንገድ መጓዘወትን እናውቃለን፡ ነገር ግን አስቀድመን ስለነቃንበዎት ያደረሱት ጉዳት ቀላል ባይሆንም ጨርሶ አላጠፋንም። ይህ ወያኔዊ ተልኮወትና ፍላጎተወት ባለመሳካቱ ግም ገማ ባሉት ሪፖረተዎት ላይ ሺፍቶች፣ የበሬ ሌቦች፤ የጠበንጃ ነጋዴወች…ወዘተ በማለት ወያኔ ከ 30 አመታት በለይ የፈጠራ ዛና በመስራት ሲደክም ኖሮ ተቀባይነት ያላገኝበትን ያረጅ ያፈጀ ስም ማጥፋት እርሰዎን ለመሰለ ሊቅ አሸክሞ ላከብን። እርሰዎ ደግሞ እንዳዲስ ግኘት ተቀብለው ለደጋፊወቸዎት ጉባኤ ሪፖርት ማሳበቂያ ማቅረበወትን ስመለከት እርሰዎ እራሰዎ ለወያኔዊ ተግባረዎ እንኳን የበሰሉ ፤ብቃት ያለወት፤ ያስተዋሉ፤ አዲስ ነገር ፈጥረው የሚያቀብሉት ጠንካራ ሰላይ አለመሆነወትን ከማሳየቱ በስተቀር አንዳችም እውነትነት የለውምና ተስፋዎትን ይቁረጡ።

ሌላው የገረመኝ የአማራ ተወካይ የምትለው ፉገራወት ደግሞ እንዴት አድርጋ አሳቀችኝ መሰለወት ? ለነገሩ ይችንም አዲስ ነገር አልፈጠሩም ! በመጀመሪያ እርሰዎ በሔዱበት ቦታ ያለው አርበኛ ሰራዊት 80 ፐርሰንቱ ከአማራው ማህበረሰብ የተፈጠረ ነው 20 ደግሞ ከተለያዩ ማህበረሰቾች የተፈጠሩ ናቸው። አማራዎቹ የበዙት እኮ የእርሰዎ ወዳጅ ወያኔዎች በአማራ ጠላትነት አብዳችሁ ከመሬቱም ከንብረቱም ከሀገሩም ከስራ ቦታውም ጠራርጋችሁ ስላባረራችሁት ነው። የወጋ ቢረሳ የተዎጋ አይረሳም ሲባል አልሰሙም እንዴ። ታዲያ ይችን የተደበቀች ካርደዎትን ይዘው ከአርበኛው ግንባር ላይ እንደሙጫ መጣበቅ አለብኝ ብለው እንቧ ከረዩ ሲሉ ከረሙ እኮ። ታዲያ ይሕንን እያወቁ ሽፍታ ወይም አማራ ለመሆን ነበር እንዴ አብሬ ካልሰራሁ እያሉ ሲያለቃቅሱ የኖሩት ? ምን ነካውት ወያኔ ስለሆኑ ተቃዋሚ መስለው እንዲሰልሉን አንፈልግም ስላልነዎት ደብቀው የያዟትን የአማራ ጥላቻ ካርደዎትን መዘዙ። ለዚህ ነው እርሰዎን አምንው ግንቦት 7 የሚሏትን የፉገራ ድርጅተዎ አባልና ደጋፊ የሆኑ ሞኝ አማራዎችን በውሸት የነፃነት ትግል ስም ሸፍነው ቂመዎትን እና ጥላቻዎትን ለመዎጣት በዎያኔ የሚያሳስሯቸው፤ የሚዘርፏቸው፤ የሚያስገድሏቸው፤ እርሰዎ በማያምኑበት ሰንደቅ አላማ አስጨብጠው የእርሰዎን ቢዝነስ የሚመቱባቸው፤ የሰብሰባ አዳራሺ ፅዳተኛ ያደረጓቸው፤ በእርሰው ወያኔዊ የክፋት ፖለቲካ መርዝ እያቀመሱ ወገናቸውን ተሳዳቢ ያደረጓቸው፤ እንዲያ ስል ደግሞ ከድርጅተዎ የሚያባርሯቸው። ለማንኛውም የአርበኞች ግንባር እርሰዎ ለሚፈፀሙት ወንጀል ሁሉ ተባባሪዎት አይደለም፡ ለመሆንም የትግል ተመክሮው አየፈቅድለትም።

በሪፖርተዎት ላይ ሲገልፁ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር የትግል ታሪክ የተበላሸ ባሕልና የአመራር ችግር እንዳለበት ለማመላከት ሞክረዋል። ነገር ግን ግንባሩን እርሰዎ በደንብ አያውቁትም እንጅ ወያኔን የመሰለ ክፉ ጠላት በአንድ በኩል እይተዋጋ በሌላ በኩል ደግሞ እንደሰዎ አይነቱን አይን ያወጣ ሰላይ እየተከላከለ አሁን ላይ የደረሰ ግንባር ነው። በግንባሩ ላይ ያልዘመተ የዎያኔ አጋር ድርጅት አይገኝም ስለዚህ እኔን አያስደንቀኝም። በሌላ በኩል የተበላሸ ባህል እንዳለውም ለማጣጣል ሞክረዋል ግና እኮ እራሱን እንደድርጅት ያቀመና ውያኔም ሆነ ሰላዮቹ በከፍተኛ ደረጃ የመትፈሩትና ስጋታችሁ ነው። እንደ ግንቦት 7 ካገኘው ጋር ለመጣበቅ ፍላጎት የለውም እንደተኮነነች ነፍስ ከእሳት ከውሐ አይዘልም። ለክቡርነተዎ ከተቀበሉኝ አንድ ምክር ልምከረዎት ተቃዋሚ መስለው ውን ውን እያሉ ተቃዋሚወችን ማፍረስና ማሰናከለዎትን ያቁሙ ከላይ እንደገለፅኩለዎት ዎዳጀወት ወያኔ በህዝባዊ አመፅ እየተናወጠ ነው በዚህ ባበቃ ሰዓት የእርሰዎ የነቀዘ የአማራ ጥላች ህብረት እያከተመለት ነው። በቀጣዮ የምገልፅለወት ስለሚኖረኝ ለዛሬው

በዚህ ላብቃ።

የወያኔ ተላላኪዎችን እናፅዳ !!
ከአርበኞቹ ግንባር ቋሬኛው ነኝ