አማራ የገጠመውን አደጋ ተደራጅቶ መከላከል ካልቻለ ሊጠፋ ይችላል

Print Friendly, PDF & Email

(Ras Hamelmal)

አማራ ሊጠፋ ይችላል። [ ይህ ሟርት አይደለም ይልቁንስ አፍጥጦ እየመጣ ያለ በመጋፈጥ እንጅ በማለባበስ ልንወጣው የማንችል ሃቅ እንጅ]

በሽታውን ያልተናገረ መድሃኒቱ አይገኝለትም ይባላል። እውነት እውነቱን እንነጋገር። ሊሆን ከሚችለው እና ጠላቶቻችን አልመው ከሚሰሩት ጉዳይ ተደብቀን ብንኖር ነገ ሃቁ ጋር ፊትለፊት መፋጠጣችን አይቀርም። እናም ዛሬ እውነት እውነቱን እያፈርጠረጥን እንነጋር። አዎ አማራ ይጠፋል። ሊያጠፉት የተነሱትን እና ሊያጠፉት ሌት ተቀን የሚሰሩትን ጠላቶቹን ለመቋቋም ጠንክሮ ካልሰራ በቀር ይጠፋል። አማራ ለምን ነው የማይጠፋው ? እጁን አጣጥፎ አጥፉኝ ብሎ ከተቀመጠ እንዴት ሊጠፋ አይችልም? ጠላቶቻቸውን አግድም እየተመለከቱ እጃቸውን አጣጥፈው የተቀመጡ ወይም የጠላቶቻቸውን መሰሪ አላማ ያልተገነዘቡ ብዙ ህዝቦች ጠፍተዋል። የአማራ እጣ ፋንታ ከነሱ የተለየ ሊሆን የሚችልበት ምን ምክንያት አለ ? የለም!

ከአማራ ወደ ትግራይ እና አፋር ተቆርጠው የተወሰዱ የአማራ ሕዝብ እና መሬቶች

ወያኔ እና ተባባሪዎቹ አማራን ለማጥፋት ቀን እና ሌት እየሰሩ ነው። በአንጻሩ እየተደረገበት ያለውን የማጥፋት ዘመቻ አይቶ እንዳላየ በማለፍ እየሆነ ካለው እና ከሚመጣው ጥፋት ለመደበቅ የሚሞክር አማራ ቁጥሩ ቀላል አይደለም። ደራሽ ጎርፍ ጠራርጎ ሊወስድህ ቢመጣ አይንህን ጨፍነህ ባለህበት ደርቀህ ብትቆም ጎርፎ ባፍጢምህ እያዳፋ ከመውሰድ ወደኋላ አይልም። ማድረግ ያለህብህ ጎርፉ ባንተ፣ በቤተሰብህ እና በንብረትህ ላይ አደጋ እንዳያስከትል አቅጣጫ ማስቀየሪያ መላ መፈለግ ነው። አልያም ጎርፉ ወደሌለበት ሸሽተህ ራስህን ማትረፍ ነው። አማራን ጠራርጎ ሊያጠፋ ያለ የጠላት ጎርፍ አሁን እየመጣ ነው። ይህን ጎርፍ የለም ብትለው አይቀርም። ይልቅ ሃይልህን አጠናክረህ ጎርፉን ወደመጣበት መመለስ መቻል አለብህ።

ዛሬ አማራ የሚባል ህዝብ ላይ በአለም ወደር የሌለው ግፍ እየተፈጸመ ነው። በትግሬ ቁጥጥር ስር ያሉ አማራ ወገኖች ግዞት ላይ ናቸው። ርስታቸውን፣ ሃብት እና ንብረታቸው ተዘርፈው ማንነታቸውን ተነጥቀው በማያውቁት ባህል በማያውቁት ቋንቋ እየተገዙ፣ በአስተርጓሚ እየኖሩ ነው። የነገ እጣ ፋንታቸው ጨርሶ መጥፋት እንደሆነ ብናውቅም ዛሬ ግን በግዞትም ቢሆን እየኖሩ ነው። በኦሮሞ ውስጥ ያሉ አማራዎች አንገታቸውን ደፍተው ያልሆኑትን ማንነት ተቀብለው፣ ሃይማኖታቸውን ቀይረው ዛሬ ነገ ህይወታችን አለፈች እያሉ የሰቆቃ ኑሮ መኖር ከጀመሩ 26 አመት ተቆጥሯል።

አሁን ያለውና የትግራይ ወያኔ በብአዴን ስም የሚያስተዳድረው የአማራ ክልል

የአማራ ርስት፣ የአማራ ታሪክ፣ የአማራ ሃብት በሙሉ ውርስ ተደርጎ በጠላት እጅ ገብቷል። በሃብቱ ባለሃብት ሆነው እየተመጻደቁበት በድህነት ማቆራመዳቸው አንሶ በድህነቱ እየተሳለቁበት ነው። ትግሬዎች ከፊሉን ጎንደር ምእራብ ትግራይ እያሉ ይጠሩታል። ከፊሉን ወሎ ደግሞ ደቡብ ትግራይ ብለው ይጠሩታል። ትግራይን ከሰሜን ሱዳን ጋር ለማገናኘት የአማራን መሬት ዳረጎት ሰጥተው ለራሳቸውም በመውሰድ አለም አቀፍ ድንበር አዘጃግተዋል። አማራ ይህን ለመከላከል አቅም እንዳይፈጥር በውስጥ ትርምስ ይጠምዱታል። በደቡብ በምእራብ እና በምስራቅ የአማራን ርስት ለፈለጉት ሁሉ አከፋፍለዋል። ይህን ሲያደርጉ ሁለት አላማ አላቸው።

1) አማራ ርስቱን ከተቀማ እንደሚዳከም ስለሚያውቁ ለማዳከም በሚል

2) ርስቴን አስመልሳለሁ የሚል ከሆነም ጠላቶቹ በዝተው እንዲነሱበት በማድረግ አማራን ማጥፋት ይቻላል ብለው ማመናቸው ነው።

አማራን እያዳከሙ ነው። አማራ ጨርሶ ከተዳከመ ኢትዮጵያ የምትባል አገር አትኖርም። ሁሉም የያዘውን ይዞ የራሱን ጎጆ ይቀልሳል። በዚህ መሃል ተቆራርሰው የሚተርፉት ወሎ፣ ሸዋ፣ ጎጃም እና ጎንደር መግቢያ መውጫ የሌለው በጠላቱ የተከበበ ህዝብ ይዘው የቀራሉ። መኖሩም በትግሬና ኦሮሞ ብሄርተኞች ይሁንታ ብቻ የተመሰረተ ይሆናል። አላማቸው ማጥፋት ነውና ይጠቅመናል ያሉትን ሁሉ ለመዘርፍ ይዘምቱበታል። ለመከላከልም አቅም ያጥረዋል። ለምን ? ቀድሞ አልተዘጋጀማ ! ቀድሞ ይሄ ይመጣል ብሎ የቤት ስራውን አልሰራማ ! ተቀራምተው ህዝቡን አጥፍተው ያሻቸውን ያደርጋሉ። የአማራ ምድር የሚባልም ይጠፋል።

በሌሎች የዱሮ አማራ ከተሞች ተበታትኖ የሚኖረው አማራም ራሱን ይክዳል። በኦሮሞ ውስጥ የሚኖረው አብዛኛው አንገቱን ደፍቶ አማራነቱን ረስቶ እና ክዶ ሌላ ማንነት ለብሶ ነው። ከዚህ በኋላ ደግሞ እንደዛ ሆኖ መኖርም የማይችልበት ሁኔታ እየመጫ ነው። በአስተርጓሚ የመኖር መብቱን ይገፈፋል። መሬቱን በሙሉ ቀምተውት ሲያበቁ መኖሪያ መሬትህን ፈልግ ብለው እንደ ሮሂንያ (Rohingya) ህዝብ ያሳድዱታል። አገሩን ርስቱን ትቶ እግሬ አውጭኝ ይላል። ግን ወዴት? አይታወቅም ! ያልተዘጋጀ እና ያልተደራጀ ህዝብ እጣ ፋንታው ይህ ነው። ስለዚህ ወገኔ አማራ ሃያል ነው። አማራን ለማጥፋት ማሰብ ከንቱ ድካም ነው እያልክ የህልም አለም አትኑር። አማራ ከአለም ህዝብ የተለየ ህዝብ አይለምና እስካልነቃ እና እስካልታገለ ድረስ ይጠፋል። የመጨረሻው አይደለም እንጅ በአሁኑ ሰአት አማራ በተጨባጭ ተገድቦ እየኖረባት ያለችው መሬት በካርታው ላይ ተቀምጣለች። ምስሉን መመልከት ይቻላል። ይህ ካልስቆጣን ምን ያስቆጣናል ? በርግጥ በዚህ መሬት ውስጥ ብአዴን በሚል ሽፋን የተቀመጠው ህወሃት የከፊል ወሎ፣ የከፊል ሸዋ፣ የከፊል ጎንደር እና ከፊል ጎጃም ህዝብ ፍዳውን እያሳየው ነው። ከፊል ከፊሎቹ በዋናው ህወሃት እና ተባባሪዎቹ መዳፍ እየተደቆሱ ይገኛሉ። ከዚህ በላይ ለመጥፋት ምልክት ሊሆነን የሚችለው ምን ይሆን ? ነው ወይስ ጨርሰን ከምድረ ገጽ ጠፍተን ምሳሌ ስንሆን ነው የሚገባን ? አባት ቅድመ አያቶቻችን በጽናታቸው፣ በትግላቸው እንጅ በምኞት እና ባዶ ጉራ አይደለም ተከብረው የኖሩት። የጠላታቸውን አመጣጥ አይተው እንደአመጣጡ እየመለሱ ነበር ይህችን ምድር ለኛ ያወረሱን።

መፍትሄው መምረር ነው። ጨከን ማለት ነው። አማራነትን ማጥበቅ ነው። ለጠላት እሬት መሆን ነው። ግንባርህን ሲልህ ግንባሩን ብለህ መሞት አለብህ። ዳር ድንበር ጥበቃ ስትዋደቅ ካንተ አልፈህ ብሄር ብሄረሰቦችን ለመጠበቅ ነበር ። ዛሬ ለራስህ የምታንስ ህዝብ ልትሆን አይገባም። ምረር !

አማራ ሆነህ እንደአማራ መደራጀት ሞት የሚመስልህ፣ የአማራ ልጅ ሆነህ በተሳሳተ ቦታ ተገኝተህ ጠላትህን የምታጠናክር፣ በአማራ ላይ የሚደረገውን ግፍ ቀለል አድርገህ የምትመለከት እና የማራ ልጆችን ትግል በፌዝ የምትመለከት ቆም ብለህ አስብ። እሳቱ ሲለበልብህ፣ አቃጥሎ ከሰል ሲያደርግህ ሳይሆን ሳትቃጠል በሞቅታው እሳት መሆኑን ልታውቅ ይገባል። ተሰብሰብ። ተሰብስበህ እሳቱን አጥፋ !

ችግሩ ገብቶኛል ብለህ በአማራ መገፋት የምትማን ሁሉ ከወሬ ወደ ተግባር ተሻገር። አንድ አንድ ጠጠር ወርውር። ከፌስ ቡክ ወሬ በዘለለ ምን ሰራሁ በል። ለመስራት ሞክር። ሞክረህ ሳይሳካልህ ቢቀር አንተ ጀግና ነህ። ግን ደግሞ ደጋግመህ ሞክር ! ይሳካልሃል።

አማራ በጠንካራ ክንዱ ጠላቶቹ ያሸንፋል።
አማራን የማጥፋት ህልማቸውን ያመክናል!

ወደፊት የሚኖረው የትግራይ ክልልና የአማራ ክልል ካርታ

ወደፊት የሚኖረው የአማራ ክልል ካርታ