የግንቦት 7 ቱባ ባለስልጣናትና የጉባዔው ታዳሚዎች በሚገኙበት የቅርብ ርቀት የተፈጸመ ግድያን … ኢሕአግ

Print Friendly, PDF & Email

የግንቦት 7 ቱባ ባለስልጣናትና የጉባዔው ታዳሚዎች በሚገኙበት የቅርብ ርቀት የተፈጸመ ግድያን በመቃወም ከኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር የተሰጠ መግለጫ!!

(clink here to read in pdf)

የሃገራችንን መሬትና ሕዝባችንን ከመከፋልና ከመበታተን አንድነቷንና ክብሯን መተኪያ የማይገኝለት ወድ ህይወቱን በመስጠት አንድ ህዝብ ፣አንድ ሃገር በሚል “እምቢኝ” ብለው ከተደላደለ የውጪ ሃገር ኑሯቸውን ጥለው በጣራራ ጸሃይ እንደ ጠላት በግንቦት 7 ከፍተኛ አመራሮች ትዕዛዝ የተገደሉ ወንድሞቻችንን ከቀጣዩ ንባብ በፊት የህሌና ጸሎት እንድታደርጉላቸው በአክብሮት እንጠይቃለን።

ከተሰኔ ወደ ሃይኮታ በሚወስደው አቅጣጫ ጉባዔው ላይ ለመገኘት በመጓዝ ላይ እያሉ በግንቦት 7 ስራ አስፈጻሚዎች ትዕዛዝ የተገደሉ ታጋይ አርበኞች!

1ኛ ታጋይ አርበኛ ተስፋ ላቀው አስረሳ ከአሜሪካ
2ኛ ታጋይ አርበኛ ይገዙ አጣናው ሽንቁጥ ከአርማጭሆ የሄደ
3ኛ ታጋይ አርበኛ ዳኜ አያሌው ከአውሮፓ ናቸው።

ከላይ ሰማቸው የተጠቀሰው አርበኞች የሃገራቸውን ነጻነት ለማየት ናፍቀው ብርዱና ረሃቡ ሳይበግራቸው ያለ ተመልካች ከተጣሉበት የአሬና በረሃ ፣የግንቦት 7 የስራ አመራሮች ከሳምንታት በፊት ጉባኤው በአሪና ይደረጋል እዚሁ ሆናችሁ ከውጪ የሚመጡትን እንግዶች ትቀበላላችሁ ተብለው እንደነበር በአሁን ሰዓት አሪናን ለቀው ለመጥቀስ በማያስፈልግ ስፍራ የሚገኙ ታጋይ አርበኛ ወንድሞቻችን የቃል ምስክርነት ተቀብለናል።

ይሁን እንጂ ቃል የተገባላቸው የጉባዔ ተሳታፊነት ምክናየቱ ሳይገለጽላቸው ወይም ሳይነገራቸው ያለምንም የአቀባበል ቦታ ዝግጅትም ሆነ የስብሰባ ቦታና ማረፊያ አለመዘጋጀት መነሻ ጥርጣሪ የገባቸው አርበኞች ከአስመራ ወደ አካባቢው ወጣ ገባ የሚሉ ግለስቦችን ያዩት ለውጥ እንዳለ ሲጠይቁ እንግዶች በጉባዔው መታደማቸውንና በጸጥታው ጥርጣሬ ምክናየት የስብሰባው ቦታ መቀየሩ ፣ በተጨማሪም ማንም የጉባኤው ታዳሚ ሞባይል ይዞ መገኘት እንደሌለበት እንደተነገራቸው ጭምር ለታጋይ አርበኞቹ ይነገራቸዋል።

በርካቶች በሁኔታው ከማዘን ባለፈ በዕልህና ቁጭት ካሉበት የጎጆ መንደር ለቀው ጉባዔ ይደረግበታል ወደ ተባለው ሃይኮታ ከተማ በመሄድ ከሚያቁንና ከምናቃቸው የጉባኤ ተሳታፊ ወንድሞቻችን በግንባር ተገናኝተን ያለውን እውነታ በግልጽ እንናገራለን በማለት ጉዞ ይጀምራሉ።
በሁኔታው የተደናገጠው የግንቦት 7 ወሬ አቀባይ መልዕክቱን ያስተላልፋል፣በተሰጠው መመሪያ መሰረትም ተጓዦቹን ለማስቆም ባደረገው ሰጣ ገባ ማስቆም ባለመቻሉ በሞባይሉ ምልዕክቱን ያስተላልፋል።

ተጠቃሾቹ ታጋይ አርበኞች ባገኙት መኪና ተንጠላጥለው አንዲት ድብቅ ሞባይላቸውን በመያዝ ጉዞ ይጀምራሉ የተጫኑበት መኪና ከጉልጅ ወጣ ብላ በምትገኘው ገርገፍ የፍተሻ ቦታ ከመድረሳቸው በፊት ወርደው በታጋይ አርበኛ ተስፋ ላቀው አስረሳ መሪነት የወሃ ኮዳቸውን ሞልተው የእግር ጉዞ ወደ ተሰኔ ያደርጋሉ።

በመንገዳቸ የሚያዩትን መኪና ሁሉ እንዲያሳፍሯቸው የእጅ ምልክት አሳይተው እንደነበርም የአካባቢው ነጋዴዎች ምስክርነታቸውን ስጥተዋል።

የሶስቱ ታጋይ አርበኞች ጉዞ በዚህ አላበቃም በየመንገዳቸው ከሚያገኙት መንደር ስንቅ የሚሆናቸውን እየጠየቁ አቧራውንና የበረሃውን ግለት አንገታቸው ላይ ባለው ሽርጥ ጭንቅላታቸውን ተጠምጥመው ያለመታከት ባንድ ላይ ያጋምሱታል።

ታጋይ አርበኞቹ ካደሩበት ከተሰኔ ወጣ ብላ ከምትገኘው መንደር በለሊት ተነስተው ስብሰባው ከሚደረግበት ሃይኮታ ከተማ መዳረሻ የእግር ጉዞ እያደረጉ እያለ እንዲቆሙ ትዕዛዝ ይሰጣቸዋል፣ለመቆም ፍቃደኛ ባለመሆናቸው በመጀመሪያው የጥይት ተኩስ ታጋይ አርበኛ ተስፋ ላቀው ተመቶ ይወድቃል፣በሁኔታው እልህ ወስጥ የገባው ታጋይ አርበኛ ይገዙ አጣናው የተባለው ከአርማጭሆ ዱር ቤቴ ብሎ ወደ ትግሉ ሜዳ ከተቀላቀለ ሁለት አመት ያልሞላው የአርማጭሆው ቆራጥ ጀግና ወደ ተኳሾቹ እያመላከተ ይጠጋል ከኋላው የነበረው ታጋይ አርበኛ ዳኜ አያሌው የታጋይ አርበኛ ተስፋ ላቀው መመታቱ ንዴት ሳይበርድለት ታጋይ አርበኛ ይገዙ አጣናው በመመታቱ መከታ ለማድረግ ወደ አቅራቢያው የገበሪዎች “ደርቢ ወይም ድንጋይ” ቤት ተንደርድሮ በመግባት ስልኩን ለቤቱ ባለቤት ሰጥቶ በዚህ ስልክ ቢደወል የደረሰብንን ሁሉ እና ፍጻሚያችን ይነገራቸው በማለት መልዕክት መንገሩን ገበሬዉና የአካባቢው ሰዎች ሶስቱም በተቀበሩበት ስፍራ ያየውንና የሰማውን እንደገለጸ ተናግረዋል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ እነኚህን እንቁ ጀግኖቻችንን ያሰገደሉም ሆነ የገደሉ ግለሰቦችና መሪዎቻቸው ጉዳዩ ተጣርቶና ተመርምሮ ከተጣራ በኋላ ለፍርድ የሚቀርቡ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር በአንክሮ የሚከታተል መሆኑን እያረጋገጥን ባካባቢው ያለው ህብረተሰብ ተባብሮና አዝኖ የጀግኖቻችንን አስከሪን ጅብ እንዳይበላው በክብር በማሳረፉ በዚህ አጋጣሚ ታላቅ አክብሮትና ምስጋና እናቀርባለን።

የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር
አንድነት ሃይል ነው!

** ማሳሰቢያ፡ በተከታታይ የወጡትን መግለጫዎች በማጣመር ዝርዝር ሁኔታ በቀጣይ የሚወጡ መሆኑን እንገልጻለን።