ከአማራ ህዝብ መደራጀት ጋር ተያይዘዉ የሚነሱ ጥያቄዎች – የአማራ ህብረት በአሜሪካ

Print Friendly, PDF & Email

ከአማራ ህዝብ መደራጀት ጋር ተያይዘዉ የሚነሱ ጥያቄዎች

 

Brochure: On the need to Organize as Amharas, in Amharic, can be downloaded :

( here )  or  ( here )

 

አማራ ለምን መደራጀት አስፈለገው? ለምን አሁን?

እንደአማራ ተደራጅተን የምንቀሳቀሰው አማራ የዘር ማጥፋት አደጋ ስለተጋረጠበት ራሳችንን ከወያኔ የዘር ማጽዳት ሂደት ለመከላከል፣ ራሳችን ከሌሎች የጥፋት ኃይሎች ለማዳን፣ ወደ ፊት ለምትፈጠረው ኢትዮጵያ አማራው የሚወከልበትን ሁኔታ ለማመቻቸት፤ እና ኢትዮጵያ እንደ አንድ ሉአላዊት ሃገር ሁና እንድትቀጥል ለማስቻል ነው።

ጋዜጠኛና አክቲቪስት ሙሉቀን ተስፋው የጥፋት ዘመን ብሎ በሰየመዉ ጥናታዊ መጽኃፍ “ጸረ አማራው የወያኔ ቡድን ንጹሐን አማሮችን እያደነ እንደጨፈጨፈ፣ ከቤት ንብረታቸው እንዳፈናቀለ፣ ሁሉም ሕዝብ በአማራ ላይ እንዲዘምት ሰነድ አዘጋጅቶና የመንግሥት በጀት በጅቶ እንደቀሰቀሰ፣ ተስፋ የሚጣልባቸውን የአማራ ልጆች እስር ቤት እያጎረ የቶርቸር ሰለባ ሲያደርግ እንደቆየ ወዘተ. ወዘተ. አይዘነጋም። በሚያሳዝን መልኩ፣ የአማራ ሕዝብ በዚህ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ መጠነ ሰፊ ውርጅብኝ ሲወርድበት የቆየ እና አሁንም ይኸው የዘር ማጥፋት ጦርነት ግልጽ በሆነ መልኩ ታውጆ የቀጠለ ቢሆንም፣ ለሕዝባችን የሚጮህለት ኃይል የለም። የሕዝባችን በደል የሚገደው ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ድርጅትም አልተገኘም።

የዚህ ነብሰ ገዳይ ቡድን ወዳጅ የሆኑ ኃያላን አገሮችም በሕዝባችን ላይ የታወጀውን የዘር ፍጅት እያዩ እንዳላዩ ማለፍን መርጠዋል። በአጭሩ ለአማራ ሕዝብ ከራሱ ውጪ ማንም እንደማይጮህለት፣ ማንም እንደማይገደው በሚገባ ተረጋግጧል።” ስለሆነም የአማራ መደራጀት ዘርፈ ብዙ ሆኖ የተደቀነብንን ፈተና ለመመከት ያስችለናል ማለት ነው።

አቶ ምስጋናው አንዱአለም ስለ አማራ መደራጀት መነሻነት ሲገልፁ “የአማራ መደራጀት መነሻው አማራው በብሔር መደራጀት አስፈላጊ ነው ብሎ ስላመነበት ሳይሆን፤ በብሔር የተደራጁ አካላት የጥቃት ሰለባ ስለሆነ እና ሌላ አማራው ራሱን የሚከላከልበት ጥግ ስላጣ ሁኔታው የፈጠረው ነው በማለት ይገልፃሉ።” በማስቀጥልም “የአማራው በአማራነቱ አለመደራጀት ለጠላቶቻችን ጉልበት ሆኖአቸዋል ሲሉ ይጨምራሉ።” ስለዚህ የአማራው መደራጀት የዚህ ሂደት ውጤት መሆኑን ተገንዝበን እና የአማራው ትግል የህልውና ትግል መሆኑን ተረድተን መደራጀታችን የግድ መሆኑን መገንዘብ ይገባናል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ መልኩ ደግሞ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ጀምሮ ወገናችን የበደል ፅዋዉ ማቆሚያ እንደሌለው ተገንዝቦ ሳይወድ በግዱ እራስን ለመከላከል ወደ ዱር ገደሉ እየተመመ ይገኛል። ይኸም ሁኔታ ለወገናችን ደጀን እንሆን ዘንድ በተለየ መልኩ በአሁኑ ሰዓት እንድንደራጅ ያስገድደናል።

የአማራው መደራጀት ከሌሎች ከአማራ ጋር ከሚኖሩ እንደቅማንት፥ አገው እና የመሳሰሉትን የሚያገል ወይም የሚጎዳ ነው ወይ?

በቅድሚያ ልንረዳው የሚገባው ነገር እነዚህ ህዝቦች አሁን ሥልጣን ያለው መንግስት የአማራ ክልል ብሎ በከለለው ይዞታ ውስጥ የሚኖሩ ናቸው። ይህም ማለት በዚያ ክልል ላይ የሚሰነዘረው ማንኛዉም ጥቃት እነሱንም አብሮ ነው የሚያጠቃው። ወያኔ የጤና ኬላ ብሎ ዘርግቶ እህቶቻችን ዘር እንዳይተኩ (መሃን) ሲደረጉ እንዚህን ህዝቦችንም ጭምር ተጠቂ ሆነዋል። በዚያ ክልል ትውልዱ የተበላሸ ትምህርት ፖሊሲ ተጠቂ ሲሆን እነዚህ ህዝቦችም ተጠቂዎች ናቸው። በኢትዮጵያ ውስጥ የመሬት ሽንሸና የተካሄደው በዚህ ክልል ብቻ ሲሆን በክልሉ ውስጥ እንደመኖራቸው እነሱም ተጎጂ ሆነዋል። ብዙ መዘርዘር ይቻላል። ከዚህ ባሻገር አማራው ከነዚህ ሕዝቦች ጋር በጋብቻና በሌሎች ማህበራዊ እሴቶች ተሳስሮ የኖረ ህዝብ ነው። የአንዱ ሃዘን ለሌላው ሃዘን፤ የአንዱ ደስታ የሌላው ደስታ ሆኖ ነው የኖረው። ስለሆነም አማራ ቢደራጅ እነዚህ ሕዝቦች የድርጅቱ ተጠቃሚ ይሆናሉ ማለት ነው። ሕዝባችን ከሌሎች የኢትዮጵያ ሕዝቦች ጋር በክፉም በደጉም አብሮ የኖረ ደግ ሕዝብ እንጂ፣ የትኛውንም ዓይነት ጭቆና የማይቀበለው የአማራ ሕዝብ ሌሎችን ሕዝቦች የጨቆነበት ጊዜ እንደሌለ ታሪክ ምስክር ነው። ማንም እንዲጨቁነን የማንፈልገውን ያህል እኛም ማንንም የመጨቆን ዓላማ የለንም፤ ኖሮንም አያውቅም።

አማራ ሆኖ መደራጀት ትዉልድን መሰረት አድርገው ከተደራጁት እንደ ጎንደር ሕብረትና ጎጃም ዓለም አቀፍ ትብብር የተለየ ምን ጠቀሜታ አለው?

ሕዝባችን እንደሕዝብ ሲጠቃ የኖረውና አሁን ሥልጣን ላይ ያለው መንግስት በደደቢት በርሃ ራሱን ሲመሰርት “የአማራ ሕዝብ ቀንደኛ የትግሬ ሕዝብ ጠላት ነው” በሚል መርህ ነው። ይህን ተከትሎም በተለያዩ የኢትዮጵያ ክልሎች ይኖሩ የነበሩ አማሮች ብዙ መከራን የተቀበሉት በትውልድ ቦታ ተለይቶ ጎንደሬ ነው፤ ጎጃሜ ነው፥ ወሎዬ ነው፥ ከሸዋ ነው ተብሎ ሳይሆን በጥቅሉ አማራ ነው በሚል ነው። ስለሆነም በአማራ ስም መደራጀት ተሰሚነታችን ከመጨመሩም ባሻገር ማንነታችን ገላጭ ነው።

የአማራው መደራጀት ከአማራ ክልል ውጭ የሚኖሩ የአማራ ሕዝቦችን ለጥቃት አያጋልጣቸዉም ወይ ?

ከአማራው ህዝብ መኖሪያ አካባቢ ውጭ የሚኖሩ አማራዎች አማራ ተደራጀም አልተደራጀም የጥቃት ሰለባ ከመሆን አልዳኑም። ይሁን እንጂ የተጠናከረ የ አማራ ድርጅት ቢኖር ኖሮ የታየው የአማራ እልቂት በእጅጉ በቀነሰ ነበር። ለታሪክም ያህል እንደሚጠቀሰው በአርሲ አርባ ጉጉ በተካሄደው የአማራ ዕልቂት ለአማራ ደራሽ በጠፋበት ጊዜ በአጭር ጊዜ ከሰሜን ሸዋ ምንጃር አማሮች ተደራጅተው ሄደው ነው ጠላቶቻቸውን የተበቀሉላችው። ከዚህ ላይ የተደራጀ የአማራ ድርጅት ቢኖር ኖሮ የቱን ያህል ወገኖቹን ይታደግ እንደነበር ሊሰመርበት ይገባል። ባለቤቱን ካልናቁ አጥሩን አይነቀነቁ እንዲሉ የአማራ መደራጀት እና መጠናከር የአማራን ዘር ሁሉ በሚኖርበት የትኛዉም የሀገሪቱ ክፍል አስከብሮትና ከሚደርስበት ጥቃት ጠብቆት እንደማንኛዉም ዜጋ በሰላም እንዲኖር ያደርገዋል እንጅ ተጠቂ ሊያደርገዉ አይችልም።

የአማራ ህዝብ ድንበር ከየት እስከ የት?

የአማራ ህዝብ ድንበር ጉዳይ ሲነሳ አንዳንድ ወገኖች የአማራን ህዝብ መደራጀት እንደ ፅንፈኞቹ ወያኔና ኦነግ የአማራን ህዝብ ከኢትዮጵያ ህዝብ ለመለየት ወይም ለመገንጠል ታስቦ የተነሳ ሃሳብ ያደርጉታል። ይሁንና የድንበር ጉዳይ የሚነሳበት ዋናዉ ምክንያት ከደርግ ዉድቀት ቡሃላ በሽግግሩ መንግስት ወያኔና ኦነግ የአማራን ህዝብ ሊወክል የሚችል ድርጅት በሌለበት ሀገሪቱን ዘርንና ቋንቋን መሰረት ባደረገ ፌደራሊዝም ሲከፋፍሏት ብዙ አግባብ ያልሆነ ከዚያም እልፍ ሲል ሀገሪቱን በፈለጉት ሽንሸና መግዛት ባይችሉ ሁለተኛዉን አማራጫቸዉን \ መገንጠልን (የወያኔን ህገ መንግስት አንቀፅ 39 ልብ ይሏል) ለመተግበር በሚያመች ሁኔታ የተሰራ ሴራ ስለሆነ የአመራ ህዝብ ይህንን የድንበር ክለላ እና “ክልል” የሚለዉን ፅንሰ ሃሳብ ህጋዊ የአማራ ተወካይ ባለበት ድጋሚ ለዉይይት ሊቀርብ ይገባል ያላግባብ የተወሰዱበት ቦታዎችም ሊመለሱለት ይገባል በማለት ነዉ።

የአማራ ህዝብ መደራጀት ከሌሎች ወያኔን እንታገላለን ከሚሉ ኃይሎች ጋር ያለዉ ግንኙነት?

የአማራ ህዝብ መደራጀት በመሰረታዊነት ራሱን ከጥፋት ማዳን ሆኖ በዚሁ ሂደት በደሙና በአጥንቱ ያቆያትን ኢትዮጵያን በጠላቶቿ ከሚደርስባት አሰቃቂ በደል ዘረፋ እና እንደ ሀገር ያለማስቀጠል(የመበታተን) ዓላማ ለመታደግም ነዉ። ይህንን ዓላማ በቅጡ ያልተረዱ አንዳንድ ወገኖች የአማራዉን መደራጀት ከኢትዮጵያ መፍረስ ፍፃሜ ጋር ያያይዙታል። ለነዚህ ወገኖች በአመራዊ ጭዋነት ደንብ መሰረት ተገቢዉ ምላሽና ማብራሪያ እየተሰጣቸዉ ሂደቱንም እየደገፉት ይገኛሉ። ይሁንና በዋናነት የአማራዉን ህዝብ መሰረት አድርገዉ (አገራዊ ወኔዉን\ ለኢትዮጵያ አንድነት ያለዉን ዘብነት እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ ምንጭነቱ ተፈልጎ) የተዋቀሩ ኢትዮጵያን ነፃ እናዎጣለን የሚሉ አንዳንድ ድርጅቶች የአማራዉ ህዝብ በማንነቱ ከተደራጀ ሊያጡት የሚችሉትን ጥቅም በማሰብ ብቻ እንደ ህዝብ የመደራጀት ሂደቱን ሊያደናቅፉ ሲሞክሩ ይታያል። ይህንን እኩይ ድርጊት ወያኔ በህዝባችንል ላይ ከሚያደርሰዉ በደል ለይተን አናየዉም።ከዚህ አድራጎታቸዉም እንዲታቀቡ አጥብቀን እንጠይቃለን።

ድል ለአማራ ህዝብ!!

የአማራ ህብረት በአሜሪካ
Amhara Association of America
መስከረም 2010 ዓ.ም /Sept. 2017/